Adam & Eve Charity Association

Adam & Eve Charity Association Our focus is to mobilize communities towards sustainable and responsible development Non profit organization

03/04/2026

“ለድሀ የሚሰጥ አያጣም፤ ዓይኖቹን የሚጨፍን ግን እጅግ ይረገማል።”
— ምሳሌ 28፥27

እሚበላ እሚሰጠን።

11/09/2025

እንኳን ለ2018 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ
ዓመቱ :- ተነስተን የሚናበራበት , የድል, የመከናወን, የስኬት, የሰላም,የደሰታ, ..... የእግዚአብሔርን ምህረት ቸርነትን የሚናይበት ዓመት ይሁንልን ።
ለእናንተ ለቤተሰቦቻቸው ለዘመድ አዝማድ ለጓደኞቻቸሁ እና ለሀገራችን ይህ ይሁን ።

አዳም እና ሔዋን የበጎ አድራጎት

26/08/2025

ሰላም ለአናንተ እና የእናንተ ለሆነው ሁሉ ላይ ይሁን ።

አዳም እና ሔዋን የበጎ አድራጎት ማህበር ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን ከመንግሥት ባገኘው ፈቃድ ከጥቅምት 30,2013 አ.ም. ጀምሮ ስራውን በይፋ እና በከፊል ጀምረናል።

አላማውም

ወላጅ አልባ ህፃናትን ማዕከል በማቋቋም በሀገራችን ብሎም በአፍሪካ የህፃናትን ህይወት በተሟላ ሁኔታ ሲለወጡ ማየትና በትምህርታዊ እና ሙያዊ ክህሎቶች በመስጠት አጠቃላይ ትምህርት ቤት ማቋቋም እና ሌሎች አገልግሎቶችን መስጠት ነው። ስንጀምር 39 ልጆች ይዘን ነበር የጀመርነው ነገር ግን ካለፉት ሁለት ኢመታት ወዲህ በገንዘብ እጥረት የምናግዛቸውን ልጆች ወደ 10 ዝቅ ለማድረግ ተገደናል።

በዚህ አመት የምናውቃቸውን እና ሊያግዙን ይችላሉ ብለን ላመንባቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች ልጆቻችንን እንዲያስተምሩልን እና የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች ማለትም፦
- ደብተር
- እርሳስ
- እስክርቢቶ
- ላጲስ
- መቅረጫ
- ቦርሳ እና ምሳ እቃ
- ዮኒፎርም ማለት ነው፡፡

የአንድ ተማሪ ወጪ በአማካኝ 10,000 ብር ነው።

ከላይ የተገለፀውን እንዲለግሱን እየጠቅን፡ እርስዎም ይህንን የነገ አገር ተረካቢ ትውልድን እንድታግዙልን በልጆቻችን ስም ጥሪያችንን እያቀረብን ለምታደርጉልን ድጋፍም በቅድሚያ በእግዚአብሔር ስም እናመሰግናለን።

ቤተልሔም ዘነበ
መስራች እና ፕሬዚደንት

04/08/2025

ያለእናንተ እገዛ መቀጠል አልቻልንም።

ሰላም ለእናንተ ቤተሰቦቻችን እንደምን ክርማችሁልናል።
ዘንድሮን ለልጆቻችን የ2018 የትምህርት ዘመን ፡ እገዛችሁን እና አብሮነታችሁን እንድታስቀጥሉልን በታላቅ ትህትና ፊታችሁ ቀርበናል። ያለእግዚአብሔር እና ያለእናንተ ፍቅር እና ድጋፍ በፍፁም ልጆቻችን ማስተማር እና የትምህርት መርጃ ማዘጋጀት አልቻልንም።
በቅድሚያ ስለምታደርጉልን እና ስለቀና ትብብራችሁ ሁሉ እግዚአብሔር ይስጥልን።

እሚያግዘን እንፈልጋለን።
10/03/2025

እሚያግዘን እንፈልጋለን።

22/02/2025

በገንዘብ እጥረት የምንደግፋቸው ወላጅ የሌላቸው ልጆች ሊበተኑብን ነው።

18/11/2024
03/10/2024

መኖር ምንድን 😡ነው ??
መሰላቸት ሆነ አይደል?

29/08/2024

ማፍረስን እሚያቆምልን ሀይል ይጥፋ፤!!

ለዘንባባ የጠነከረ ህግ ለዚች እንቦቃቅላ መሆን ሲያቅተው ማየት እጅግ ያማል!😭እስከ መቼ ነው ታስሮ የሚቀለብ መንጋ ተመጣጣኝ ባልሆነ ቅጣት በየእስር ቤቱ የምንሰበስበው?ህግ አውጪውና አስፈፃሚ...
18/08/2024

ለዘንባባ የጠነከረ ህግ ለዚች እንቦቃቅላ መሆን ሲያቅተው ማየት እጅግ ያማል!😭

እስከ መቼ ነው ታስሮ የሚቀለብ መንጋ ተመጣጣኝ ባልሆነ ቅጣት በየእስር ቤቱ የምንሰበስበው?

ህግ አውጪውና አስፈፃሚው አካል ህጉን ይቀይርልን!!!

ልጆቻችንን ማሳደግ የማንችልበት ሀገር እየኖረን ነውና ሁላችንም ድምፃችንን እናሰማ!!

Address

Koteb
Addis Ababa
80778

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Adam & Eve Charity Association posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Adam & Eve Charity Association:

Share