የወግዲ ልማት ማህበር_Wogide Development Association

የወግዲ ልማት ማህበር_Wogide Development Association ልማት ማህበር

21/04/2023

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1444ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ።
መልካም በዓል!

18/03/2023

ሰላም እንዴት ናችሁ የገፃችን ተከታዮች?
እንደሚታወቀው በወግዲ ወረዳ መነሃሪያ አካባቢ በተከሰተ የእሳት አደጋ ንብረታቸው የወደመባቸውን ሰዎች በተንቀሳቃሽ ምስል አጋርተን ነበር ።
እናም ይህንን ጉዳት ለማገዝ እዚያው ወረዳው ላይ በሚንቀሳቀሱ መልካም ሰዎች አማካኝነት የገቢ ማሰባሰቢያ እንቅስቃሴ እያደረጉ ኮሚቴ ተቋቁሞ የባንክ ደብተር ተከፍቶ እርዳታ ማሰባሰቡ ቀጥሏል።ሂደቱም እጅግ በጣም ደስ የሚል ነው።
ቡዚህ መልካም ስራ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የባንክ አካውንት በቴሌግራም ገፃችን የለቀቅን ስለሆነ ገብታችሁ ማየት ትችላላችሁ።
ሌላው ይህ እንቅስቃሴ ወደተሻለና ዘላቂ ወደሆነ ስራ ለማስቀጠል በመነጋገር ላይ ስላለን ሃሳባችሁን ታካፍሉን ዘንድ ጋብዘናችኋል።

15/03/2023
ከዚህ በፊት እንደገለፅኩት ፦ገፁ የወደፊት እቅድ እንጅ የተመሰረተ እንዳልሆነ መግለፄ ይታወቃል።ከፅሁፉ ያልተረዱኝ አንዳንድ ወንድሞችና እህቶች በውስጥ ምን ልትመሰርት አስበህ ነው ?የሚል ጥያ...
15/04/2022

ከዚህ በፊት እንደገለፅኩት ፦
ገፁ የወደፊት እቅድ እንጅ የተመሰረተ እንዳልሆነ መግለፄ ይታወቃል።
ከፅሁፉ ያልተረዱኝ አንዳንድ ወንድሞችና እህቶች በውስጥ ምን ልትመሰርት አስበህ ነው ?የሚል ጥያቄ በተደጋጋሚ እያቀረቡልኝ ይገኛል።
መልሴ ምንም ነው።ምክንያቱም የሚመሰረተው ማህበር ገና ለውይይት የቀረበ ነው።ሲመሰረትም በግለሰብ ደረጃ የሚቋቋም ሳይሆን መሪ ተመርጦለት ሰብሳቢ ...ተመርጦለት በብዙ ሰዎች ስብስብ የሚቋቋም መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል።
ለውይይት ይረዳ ዘንድ ይህን የቴሌግራም ቻናል ከፍቻለሁ።

https://t.me/wogededevelopmentalassociation

♥ ሌላው በኮመንት ብዙ አስተያየቶች መጥተዋል ።በጥቂቱ ፦አመራሩ ሌባ ነው እንደት ልንመሰርት እንችላለን?
ብር ሰብስባችሁ ልትበሉ አስባችሁ ነው።
መቼም ወግዲ አትለወጥም እና ሌሎች አስተያየቶች ተሰጥተዋል።
ይህ ማህበር መግባባት ላይ ተደርሶ ቢመሰረት ከማንኛውም ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት ነፃ እንደሚሆን ልናምን ይገባል።ስለዚህ ማንኛውም የፖለቲካ አመራር ማህበሩ ውስጥ ሊካተት አይችልም ያ ማለት በነፃነት ይንቀሳቀሳል ማለት ነው።

♥ በተጨማሪም ማህበሩ ሲመሰረት የራሱ የሆነ ህግ ይኖረዋል ።ህጉ ማህበሩን የሚመሩትም ሆኑ አባላቶች ህጉን ከተላለፉ በህግ ተጠያቂ ይሆናሉ ማለት ነው። ህግ ሲወጣለት የገንዘብ ብክነትን የስነ ምግባር ጉድለትንም ጭምር ማዕቀፍ አድርጎ የሚወጣ ይሆናል።ህግ ሲረቀቅም የህግ ባለሙያዎችን በማማከር እንጅ በዘፈቀደ አይሆንም ።ማህበሩም ሲቋቊም እንድሁ።

ትኩረት ልንሰጥበት የምንችለው ጉዳይ ደግሞ በወረዳው የመልማት ጉዳይ ላይ ተስፋ ማሟጠጥ ነው።
ይህ ፈፅሞ ስህተት ነው።እኔ እስከማውቀው ድረስ ልማታዊም ሆነ መረዳጃ ማህነራት ተመስርተው አልሰምር ብሏቸው የተበተኑ የሉም።ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ተስፋ መቁረጡ ተገቢ አይደለም።
በአመራር ችግር ምክንያት የተስተጓጎለው ልማት በልጆቿ ይስተካከላል የሚል አቋም ልንይዝ ይገባል።

ሌላው የአመራር ችግር ያለበት ወግዲ ወረዳ ብቻ እንደሆነ አድርጎ ማሰቡ ተገቢ አይደለም። እንደ አጠቃላይ በክልል ደረጃ የአመራር ችግር እንዳለ ግንዛቤ ውስጥ ልናስገባ ግድ ይለናል።
ይህንንም የአመራር ችግር ተቋቁመው ማህበራት የመሰረቱ ወረዳዎች ብዙ ናቸው።ለምሳሌ በቅርቡ የመቅደላ ወረዳ ተወላጆች ማህበር መስርተዋል ።
ስለዚህ እኛ ማድረግ የማንችልበት ምንም ምክንያት የለም።

ደስ የሚለው ደግሞ እጅግ አበረታችና ሞራል የሚሰጡ አስተያየቶች አሉ። እየወደቅን እየተነሳንም ቢሆን ወደተግባር እንግባ የሚሉ አስተያየቶች አሉ ይህ ይበረታታል።
ከላይ የፃፍኩት የኔ የግሌ ሀሳብ ነው።ማንኛውንም አስተያየት መስጠት ይቻላል።ስጋቶች መነሳታቸው ለጥንቃቄ ጠቃሚ ስለሚሆኑ የሚነሱ ስጋቶች በግልፅ ቢነሱ መልካም ነው።
አመሰግናለሁ!

You can view and join right away.

ሰላም ሰላም እንደት ናችሁ ውድ የወግዲ ተወላጆች እንድሁም ወዳጆች።እንደሚታወቀው ይህን ገፅ የከፈትኩት ማህበሩ ተመስርቶ ሳይሆን ለውይይት እንደሆነ አሳውቄ ነበር።በኮመንት ላይ ብዙ ገምቢ አስ...
14/04/2022

ሰላም ሰላም እንደት ናችሁ ውድ የወግዲ ተወላጆች እንድሁም ወዳጆች።
እንደሚታወቀው ይህን ገፅ የከፈትኩት ማህበሩ ተመስርቶ ሳይሆን ለውይይት እንደሆነ አሳውቄ ነበር።
በኮመንት ላይ ብዙ ገምቢ አስተያየቶች አሉ በተመሳሳይ ካለው ነባራዊ ሁኔታ በመነሳት ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ያዘሉ አስተያየቶች ተመልክቻለሁ።
ለሁሉም አስተያየቶች እያመሰገንኩ ለውይይት ይመቸን ዘንድ ይህን የቴሌግራም ግሩፕ ከፍቻለሁ።በመሆኑም ይመለከተኛል የሚል አካል ወደግሩፑ መቀላቀልና ሀሳቡን ማጋራት ይችላል።

11/04/2022

ሰላም የገፁ ተከታዮች
የወግዲ ተወላጅ እንድሁም ወዳጅ ዘመድ የሆናችሁ ይህ የወግድ ልማት ማህበር የሚለው ገፅ የተከፈተው ማህበሩ ተቋቁሞ እንዳልሆነ ለማሳወቅ እወዳለሁ።
ገፁን የመሰረትኩት ለውይይት ያመቸኝ ዘንድ ስለሆነ በሀሳቡ የተሻለ አስተያየት ያላችሁ ሰዎች እንዳላችሁ በመመን ነው።
ብዙ የተሰወረ ባይሆንም በብዙ አካባቢዎች በወረዳ ደረጃ ጭምር የመረዳጃና የልማት ማህበር አቋቁመው ዘርፈ ብዙ ችግሮቻቸውን እየፈቱባቸው ይገኛል።
ይህንን በጎ ሀሳብ የምትደግፉ ግለሰቦች ሀሳባችሁን ያለ ስስት በመለገስ ወደ ትግበራው ብንሄድ የሚል የግል አስተያየት አለኝ።
ማህበሩ ሲመሰረት ብዙ ችግሮችን እንደምንፈታበት ምንም ጥርጥር የለኝ።
በቀላሉ እንኳን የችግርተኛ ቤተሰብ ተማሪዎችን በከፊል በዘላቂነት መርዳት አቅመ ደካሞችን መርዳት...ሌላው ጥቅሙ በማህበሩ አማካኝነት እየተገናኙ ብዙ ውይይቶችን ማድረግ ከዛም ከሚመለከተው አካል ጋር ለመፍትሄ መቀመጥ ለውጥም ማምጣት ይቻላል።
በቅርቡ የቴሌግራም ግሩፕ ከፍቼ የማሳውቃችሁ ይሆናል እስከዚያው ግን ኮመንት ላይ ሀሳባችሁን እንድታስቀምጡ በአክብሮት እጠይቃችኋለሁ።
አመሰግናለሁ!

Address

Addis Ababa
Addis Ababa
WWW.WOGIDEDEVELOPMENTALASSOCIATION.ET

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የወግዲ ልማት ማህበር_Wogide Development Association posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የወግዲ ልማት ማህበር_Wogide Development Association:

Share