እንስሳትም ትኩረት ይሻሉ

እንስሳትም ትኩረት ይሻሉ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from እንስሳትም ትኩረት ይሻሉ, Charitable organisation, Addis Ababa.

Animals need attention is a charity fighting for animals right, promote responsible pet ownership , creating community awarness, shelter, medical treatment,Implementing spay and neuter,rescuing ,promote animal welfare .
1000401963042

Feven Melese አሳክተነዋል  💪
20/07/2026

Feven Melese
አሳክተነዋል 💪

ለነገ በትራንስፖርት የሚያግዘን አለ?ሁለቱ 🐕🐕ች አስቸኳይ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ስለሆኑ አይተን ማለፍ አልቻልንም 🥺ነጯ ቦሌ አራብሳ በመኪና አደጋ ምክንያት መንጋጋዋ የተነቀለ አፏን መዝጋት...
16/07/2026

ለነገ በትራንስፖርት የሚያግዘን አለ?
ሁለቱ 🐕🐕ች አስቸኳይ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ስለሆኑ አይተን ማለፍ አልቻልንም 🥺

ነጯ ቦሌ አራብሳ በመኪና አደጋ ምክንያት መንጋጋዋ የተነቀለ አፏን መዝጋት የማትችል።

አንዱ ሀያ ሁለት አካባቢ ትልቅ እጢ የተሸከመ።

ስለዛ ትራንስፖርት ምንፈልገው ከቦሌ አራብሳ እና ከ22 ውሾቹ ተነስተው cmc ሚካኤል ለሰርጀሪ ሚገቡበት ክሊኒክ ነው ሲጨርሱ ወደ ሼልተር ይወሰዳሉ።

ለሁለቱ ሙሉ ቀን ይፈጃል። በፈቃደኝነት መተባበር የሚችል ካለ ያሳውቀኝ 🙏

Is there anyone who can help us with transportation tomorrow?

These two dogs 🐕🐕 urgently need medical attention, and we simply couldn't walk away after seeing their condition. 🥺

🤍 The white dog is in Bole Arabsa. She was hit by a vehicle, and her jaw has been dislocated. She cannot close her mouth.

🐕 The second dog is in the 22 area and is carrying a large tumor that requires urgent surgical treatment.

We are looking for transportation to:

- Pick up the white dog from Bole Arabsa and the second dog from 22.
- Take both dogs to the veterinary clinic near CMC Michael for surgery.
- After their procedures, transport them to our shelter.

This will require a vehicle for the entire day.

If you are able to volunteer your vehicle and time, or know someone who can, please let me know. Your support could save two lives. 🙏
አልዓዛር አየለ የዉቤ ልጅ
ማገዝ ምትችሉ መልእክት አስቀምጡልኝ
Feven Melese

12/07/2026

Interview with BBC AFRICA
እንስሳትም ትኩረት ይሻሉ
Feven Belete

08/07/2026

በሆሳዕና ከተማ የተደረገውን አሰቃቂ የውሾች ጅምላ ገደላ ወደሶሻል ሚድያ አምጥቶ ከማጋለጥ ጀምሮ እንዲቆም እስከማስደረግ ጉዳዩ ከኢትዮጵያ አልፎ አለም አቀፍ ሚድያዎችን ተሳታፊ ያደረገ ጉዳይ እንዲሆን በማስቻል ተሳክቶልናል 🤗
በዚህ የተቃውሞ ካምፔይን ላይ የተሳተፋችሁትን በሙሉ አመሰግናለሁ 🙏🐾🙏

08/07/2026

በ #ሆሳዕና ከተማ በእብድ ውሻ በሽታ ምክንያት ነዋሪዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ውሾቻቸውን ለመግደል ተገደዱ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሆሳዕና ከተማ ከእብድ ውሻ በሽታ ጋር በተያያዘ የሦስት ሕፃናት ሕይወት ማለፉንና በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ሆስፒታል መግባታቸውን ተከትሎ፤ ነዋሪዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ የራሳቸውን ውሾች ለመግደል መገደዳቸውን ቢቢሲ ዘገበ።

የዜና ወኪሉ እንደዘገበው፤ ነዋሪዎች ውሾቻቸውን እንዲገድሉ፣ ካልሆነ ግን እስከ 50 ሺህ ብር የሚደርስ ቅጣት እና እስራት እንደሚጠብቃቸው መመሪያ ተላልፏል። ይህ መመሪያ ውሾቹ ክትባት የወሰዱ ቢሆንም እንኳ ተግባራዊ እንደሚሆን ተገልጿል። የዓይን እማኞች እንደተናገሩት አንዳንድ የውሻ ባለቤቶች ውሾቻቸውን በገመድ አንቀው ወይም ደብድበው የገደሉ ሲሆን፣ ሌሎች ደግሞ እንዲገደሉ አሳልፈው ሰጥተዋል።

የአካባቢው ኃላፊዎች እንደገለጹት እርምጃው የተወሰደው ከበሽታው ጋር በተያያዘ ተከታታይ የሰዎች ሞት ከተመዘገበ በኋላ ነው። የከተማዋ ከንቲባ ሳሙኤል ሽጉጤ ወረርሽኙ የሦስት ሕፃናትን ሕይወት የቀጠፈ መሆኑና ወደ 80 የሚጠጉ ሌሎች ሰዎችን ደግሞ ለሆስፒታል መዳረጉን አስታውቀዋል። ከንቲባው አክለውም በከተማዋ ካሉ 10 ሺህ ገደማ ውሾች ውስጥ 70 በመቶ ያህሉ የእብድ ውሻ በሽታ ክትባት ወስደው እንደነበር ገልጸዋል።

የእንስሳት ሕክምና ባለሙያዎች እና የደኅንነት ተሟጋቾች ይህንን የጅምላ ግድያ አጥብቀው ኮንነዋል። ቢቢሲ የጠቀሳቸው የእንስሳት ሐኪሙ ዶክተር አልዓዛር አየለ በድርጊቱ «በጣም ማዘናቸውን» ገልጸው፤ በጥቂት ቀናት ውስጥ ብቻ ከ400 እስከ 450 የሚደርሱ ውሾች መገደላቸውን ገልጸዋል። ዶክተር አልዓዛር «ሰዎች ውሾችን እየጎተቱ በማውጣት በሚዘገንን ሁኔታ ገድለዋቸዋል። ይህ በሃይማኖት፣ በባህልና በሕግ ተቀባይነት የሌለው እና ኢ-ሞራላዊ ድርጊት ነው። ተንቀሳቃሽ ምስሎች (ቪዲዮዎች) የውሻ ባለቤቶች ውሾቻቸው ሲገደሉባቸው እያለቀሱ እንደነበር ያሳያሉ» ብለዋል።

በአዲስ አበባ የእንስሳት መጠለያ ያላትና የመብት ተሟጋች የሆነችው ፈቨን መለሰ በበኩሏ ለቢቢሲ እንደተናገረችው፤ ምንም እንኳ አሁን ላይ ግድያው መቆሙ ቢነገርም በአንዳንድ አካባቢዎች በባለቤቶች ላይ የሚደረገው ተጽዕኖ ቀጥሏል። ፈቨን «ግለሰቦች አሁንም ድረስ ቤት ለቤት እየተዘዋወሩ ሰዎች ክትባት ያልወሰዱ ውሾቻቸውን እንዲያስወግዱ እየጠየቁ ነው» ስትል፣ ድርጊቱ ከአስተዳደሩ ቁጥጥር ውጭ ሊወጣ እንደሚችል አስጠንቅቃለች።

የፈቨን ድርጅት የጅምላ ግድያን በማስቀረት የተቀናጀ የክትባት እንዲካሄድ እና ሰብአዊነት የተሞላበት የውሾች ቁጥር መቆጣጠሪያ ስልቶች እንዲተገበሩ ጥሪ ከሚያቀርቡት መካከል አንዱ ነው።

የአካባቢው ባለሥልጣናት ግድያው ሕገ-ወጥ መሆኑንና በአስተዳደሩ በይፋ የታዘዘ አለመሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ ከንቲባ ሳሙኤል ፖሊስ በጉዳዩ ላይ ምርመራ እንዲያደርግ መመሪያ መሰጠቱን መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል።

የእንስሳት ደኅንነት ተሟጋች ቡድኖች እንደሚሉት ይህ አጋጣሚ በአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች ሥርዓታዊ የሆነ የእብድ ውሻ በሽታ መቆጣጠሪያ እና ሰብአዊነት የተሞላበት የእንስሳት አያያዝ ፖሊሲዎች አለመኖራቸውን እንዲሁም የክትባት እና መሰል ፕሮግራሞች እጅግ ውስን መሆናቸውን በግልጽ ያሳየ ነው።

Address

Addis Ababa
1000

Telephone

+251913585438

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when እንስሳትም ትኩረት ይሻሉ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to እንስሳትም ትኩረት ይሻሉ:

Shortcuts

Share