የኢትዮጵያውያን ድምጽ - Ethiopian Voice

የኢትዮጵያውያን ድምጽ - Ethiopian Voice This is Ethiopian Voice!
ይህ የኢትዮጵያውያን ድምፅ ነው!

መረጃዎትን በውስጥ ይላኩልን!

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን! ሙፍቲ ሀጅ ዑመር ወደ ማይቀረው አለም ወደ አኺራ ተሻግረዋል! አላህ በእዝነቱ ይቀበላቸው!ጌታችን አላህ ያሻህን ሰሪ ነህና ሸኻችንን ወደአንተ ወሰደሀቸዋል! ...
19/10/2025

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!
ሙፍቲ ሀጅ ዑመር ወደ ማይቀረው አለም ወደ አኺራ ተሻግረዋል! አላህ በእዝነቱ ይቀበላቸው!
ጌታችን አላህ ያሻህን ሰሪ ነህና ሸኻችንን ወደአንተ ወሰደሀቸዋል! በራሕመትህ ተቀበላቸው። ከመልካሞቻቸው አብዛላቸው፣ ከወንጀሎች በመሐርታህ አንፅተሀቸው በጀነትህ አኑራቸው!
ﺍﻧﺎ ﻟﻠﻪ ﻭﺍﻧﺎ ﺍﻟﻴﻪ ﺭﺍﺟﻌﻮﻥ !!!
ﻧﺴﺎﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻥ ﻳﻐﻔﺮ له ﻭﻳﺮﺣﻤه ﻭﻳﺠﻤﻌﻨﺎ ﺑﻪ ﻓﻲ ﺍﻟﻔﺮﺩﻭﺱ ﺍﻻﻋﻠﻰ !
ﻋﻈﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﺟرهم!

መስጅድ ገብቶ የጨፈጨፈው ፋኖ ፕሮፓጋንዳ!‼️             (ዐብዱልጀሊል ሸኽ ዐሊ ካሣ)                    ★★★//💢//★★★ በመካነ ሰላም መስጊድ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ ለመ...
07/10/2025

መስጅድ ገብቶ የጨፈጨፈው ፋኖ ፕሮፓጋንዳ!‼️
(ዐብዱልጀሊል ሸኽ ዐሊ ካሣ)
★★★//💢//★★★

በመካነ ሰላም መስጊድ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ ለመሸፈን የተዘረጋ የጥላቻና የማታለል ኔትዎርክና ታክቲክ

በደቡብ ወሎ መካነ ሰላም ከተማ በሚገኘው መስጅደ ኑር ውስጥ በዒሻ ሰላት ላይ በነበሩ ኢማም፣ የመስጂድ አገልጋዮች እና የእስልምና ጉዳዮች አመራሮች ላይ በፋኖ ታጣቂዎች የተፈጸመው ጭፍጨፋ፣ በዘመናችን ካሉ የጦር ወንጀሎች ጋር የሚመደብ አሰቃቂ ድርጊት ነው። ይህ ድርጊት በራሱ የከፋ ወንጀል ሆኖ ሳለ፣ ወንጀሉን ለመደበቅ፣ ለማስተባበልና የጥቃቱን ሰለባ የሆነውን ህዝበ ሙስሊም በድጋሚ ለመናቅና ለማታለል የተሰሩት የፕሮፓጋንዳ ስልቶች፣ የፋኖን እንቅስቃሴ ምንነትና የወደፊት አደጋውን በግልጽ ያሳያሉ።

በፋኖ እና በልሳናቱ እየተሰራ ያለው ፕሮፓጋንዳ ከእስራኤል እና ከሌሎች የጦር ወንጀል ፈጻሚዎች የፕሮፓጋንዳ ስልቶች ጋር በማነጻጸር የፋኖ ፕሮፓጋንዳ የጦር ወንጀለኞችን መደበኛ ስልቶች እንዴት እንደተከተለ፣ ህዝበ ሙስሊሙን ምን ያህል እንደናቀ እና ለወደፊት ጥቃቶች መንገድ እንዴት እያመቻቸ እንደሆነ መረዳት ተገቢ ነው።

💢የጦር ወንጀልን ለመሸፈን የሚነዙ ፕሮፓጋንዳዎች፡

በጦርነት ወቅት የሚፈጸሙ ጭፍጨፋዎችና የጦር ወንጀሎች ሁልጊዜም በጠንካራ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ይታጀባሉ። ዓላማው ወንጀለኞቹን ከተጠያቂነት ማዳን፣ የደጋፊዎችን ሞራል መጠበቅ፣ የገለልተኛ ታዛቢዎችን አእምሮ ማወክ እና የተጎጂውን ማህበረሰብ የበለጠ ማሸማቀቅ ነው።

እነዚህ ፕሮፓጋንዳዎች በሚከተሉት ዋና ዋና ስልቶች ላይ የተመሰረቱ ናቸው፡

1️⃣ የመካድ ስልት (Denialism): ወንጀሉ መፈጸሙን ሙሉ በሙሉ ማስተባበል ነው። ይህ የመጀመሪያው የመከላከል መስመር ሲሆን፣ ማስረጃዎች ገና ሳይሰባሰቡና ሳይሰራጩ ሲቀሩ ውጤታማ ሊሆን ይችላል።

2️⃣የማጽደቅና የማስተባበያ ስልት (Justification and Rationalization): ወንጀሉ መፈጸሙ ሲታወቅና መካድ በማይቻልበት ጊዜ፣ ድርጊቱን "አስፈላጊ" እና "ህጋዊ" ለማስመሰል የሚደረግ ጥረት ነው።

ይህ "ጠላት በቅዱስ ስፍራ መሽጎ ነበር"፣ "እነሱም ጥቃት ፈጽመዋል"፣ "የተገደሉት ንጹሀን ሳይሆኑ ተዋጊዎች ናቸው" የሚሉ ትርክቶችን ያካትታል። ይህ በወታደራዊ ቋንቋ "የዒላማን ሰብዓዊነት መግፈፍ" (Dehumanization of the Target) በመባል ይታወቃል። ሰለባዎቹን ወደ "ህጋዊ ወታደራዊ ዒላማነት" በመቀየር ወንጀሉን ህጋዊ ለማስመሰል ይሞክራል።


ናዚ ጀርመን: አይሁዶችን ከማጥፋታቸው በፊት "የጀርመን ጠላቶች"፣ "ተንኮለኞች" እና "ሰብዓዊ ያልሆኑ" በማለት ሰብዓዊነታቸውን በፕሮፓጋንዳ ገፈዋል። ምኩራቦችን (synagogues) "የሴራ ማዕከላት" በማለት ለጥቃት ህጋዊ ሽፋን ይሰጡ ነበር።

እስ&ራኤል: በፍልስጤም ላይ በምትፈጽማቸው ጥቃቶች፣ በተደጋጋሚ ትምህርት ቤቶችን፣ ሆስፒታሎችን እና መስጊዶችን በቦምብ ስታወድም የምትሰጠው ዋነኛ ምክንያት "የሃ£ማስ ታጣቂዎች ተጠልለውበታል" ወይም "የጦር መሳሪያ ማከማቻ ነው" የሚል ነው። ይህ በመካነ ሰላም መስጊድ ላይ የቀረበውን ምክንያት በትክክል ያንጸባርቃል።

3️⃣ የማንነት ማጠብ (Identity Laundering) እና የማካተት ቅዠት (Illusion of Inclusion): ወንጀሉ የተፈጸመው በዘር ወይም በሃይማኖት ጥላቻ መሆኑን ለማስተባበል፣ አጥቂው ቡድን በውስጡ ከተጠቂው ማህበረሰብ የተውጣጡ "ተወካዮች" እንዳሉት አድርጎ ያቀርባል። ይህ "ቶኬኒዝም" (Tokenism) በመባል የሚታወቅ ሲሆን፣ "እኛም ሙስሊሞች/የእናንተ ወገኖች አሉን፣ ስለዚህ ድርጊቱ ፀረ-ሙስሊም/ፀረ-ወገን ሊሆን አይችልም" የሚል የተሳሳተ አመክንዮ ለመፍጠር ያገለግላል።

4️⃣ የትርክት ቁጥጥርና መስረቅ (Narrative Control and Hijacking): የተጎጂውን ማህበረሰብ ምልክቶች፣ ጀግኖች እና ትርክቶች በመውሰድ ለራስ ፕሮፓጋንዳ ማዋል ነው። ይህ እጅግ የከፋ የንቀት ምልክት ሲሆን፣ የተጎጂውን ህመምና ታሪክ በመስረቅ ለገዳዩ ዓላማ ማዋልን ያመለክታል።

💢 የፋኖ ፕሮፓጋንዳ ስልቶች የትኞቹን ተጠቀመ

በመካነ ሰላም መስጅደ ኑር ከተፈጸመው ጭፍጨፋ በኋላ የፋኖ ወገኖች የተጠቀሟቸው ፕሮፓጋንዳዎች ከላይ ከተዘረዘሩት የጦር ወንጀለኞች መደበኛ ስልቶች ጋር አንድ ለአንድ ይጣጣማሉ።

✅አንደኛ እና ሁለተኛ፡ ከመካድ ወደ ማጽደቅ - የእስራኤል እና የናዚ ታክቲክ ድግግሞሽ

የፋኖ የመጀመሪያ ምላሽ ጭፍጨፋውን መካድ ነበር። ይህ የተለመደ የድንጋጤ ምላሽ እና ማስረጃን የማጥፋት ሙከራ ነው። ሆኖም፣ እውነታው በምስክሮችና በማስረጃዎች መውጣት ሲጀምር፣ በፍጥነት ወደ ሁለተኛው ስልት ተሸጋገሩ፤ ይኸውም "ግድያውን አምኖ ማጽደቅ" ነው።

* ፕሮፓጋንዳው: "ግድያው የተፈጸመው መስጂዱ ውስጥ የጠላት ኃይል (መከላከያ፣ ሚሊሻ) ስለመሸገ ነው" የሚለው ትርክት፣ ከእስራኤል የጦር ኃይል የፕሮፓጋንዳ መዝገብ በቀጥታ የተቀዳ ነው። እስ£ራኤል ጋዛ ውስጥ የአል-ሺፋ ሆስፒታልን ስትደበድብ "የሃማስ ኮማንድ ማዕከል ነው" እንዳለችው ሁሉ፣ ፋኖም መስጅደ ኑርን "የጠላት ምሽግ" በማለት ወንጀሉን ወደ "ህጋዊ ወታደራዊ እርምጃ" ለመቀየር ሞክሯል።

ይህ ስልት፡
1. ወንጀሉን ወደ ህጋዊ የጦርነት ምት ቀይሮታል፤
2. ሰለባ የሆኑትን ኢማምና ምዕመናን "ተዋጊዎች" በማለት ሰብዓዊነታቸውን ገፏል፤
3. መስጂዱን፣ የሰላምና የአምልኮ ቦታ መሆኑን በማሳጣት "ወታደራዊ ምሽግ" የሚል ስያሜ ሰጥቶታል።

ይህ ፕሮፓጋንዳ፣ በመስጂዱ ውስጥ ምንም አይነት የመንግስት ኃይል አለመኖሩ እየታወቀ መሰራጨቱ፣ ድርጊቱ ሆን ተብሎ በንጹሀን ላይ ያነጣጠረ መሆኑንና ፕሮፓጋንዳውም ይህን ለመሸፈን የተፈጠረ ውሸት መሆኑን ያጋልጣል።

✅ ሶስተኛ፣ አራተኛ እና አምስተኛ፡ የማንነት ማጠብ እና የማታለል ስልቶች

እነዚህ ሶስት ነጥቦች አንድ ላይ ሲታዩ፣ የፋኖን "የማንነት ማጠብ" (Identity Laundering) ዘመቻ ያሳያሉ። የጥቃቱ ዋነኛ ሰለባዎች ሙስሊሞች ሲሆኑና ድርጊቱም በአምልኮ ቦታቸው ላይ ሲፈጸም፣ ትግሉ "ፀረ-ሙስሊም" እንዳይመስል ለማድረግ የተነደፉ ናቸው።

🌑 "ትግሉ ሃይማኖታዊ አይደለም፤ የምንታገለው ለአማራ ሙስሊሞችም ነው" (ፕሮፓጋንዳ 3): ይህ "የሚያብረቀርቅ አጠቃላይነት" (Glittering Generality) በመባል የሚታወቅ የፕሮፓጋንዳ ስልት ነው። ድርጊቱ ከሚናገረው በተቃራኒ፣ የሙስሊም ቃላትን "አደም፣ አኢሻ፣ ወላሂ ወዘተ" በመጠቀም አዎንታዊ ስሜት ለመፍጠር ይሞክራል። መስጂድ ውስጥ ሙስሊሞችን እየገደሉ "ትግላችን ለሙስሊሞችም ነው" ማለት፣ የተግባርና የቃል ግጭት የታየበት የንቀት ጥግ ነው።

🌑 "ሙስሊም" ፋኖዎችን እንደ ምስክር ማቅረብ (ፕሮፓጋንዳ 4 እና 5): "ፕራክቲካል ሙስሊም ያልሆኑ" ወይም የሙስሊም ስምና ልብስ ያላቸውን ግለሰቦች በማቅረብ "እኛም ሙስሊሞች ነን፣ ድርጊቱ ትክክል ነበር" እንዲሉ ማድረግ፣ "ቶኬኒዝም" እና "የሀሰት ምስክርነት" (False Testimonial) ማሳያ ነው። ይህ ስልት፡
1. ከውስጥ የመጣ ድጋፍ እንዳለ ያስመስላል፤
2. የሙስሊሙን ማህበረሰብ ለመከፋፈል ይሞክራል ("እነሱም እኮ መስክረዋል")
3. የድርጊቱን ፀረ-እስልምና ገጽታ ለማደብዘዝ ይሞክራል።

በሙስሊም ስም የሚጽፉ፣ ጺም አስረዝመው ጥምጣም ያሰሩ ግለሰቦችን እንደ "ሙስሊም ተዋጊ" ማቅረብ፣ የፕሮፓጋንዳውን ጥልቀትና የማታለል ደረጃ ያሳያል። ይህ ህዝበ ሙስሊሙን የማሰብ ችሎታ የሌለውና በውጫዊ ገጽታ ብቻ የሚታለል አድርጎ ከመቁጠር የመነጨ የንቀት ተግባር ነው።

✅ስድስተኛ፡ የትርክት ስርቆት - የሙስሊሙን ህመም ለገዳዩ ዓላማ ማዋል

ይህ ከሁሉም በላይ የከፋውና የፋኖ ፕሮፓጋንዳ የደረሰበትን የሞራል ዝቅጠት የሚያሳየው ስልት ነው። እዚህ ላይ የቀረቡት መረጃዎች የፕሮፓጋንዳውን እኩይነት የበለጠ ያጋልጣሉ።

🩸የሙስሊም ጀግኖችንና ሰማዕታትን፣ የወሎ እስልምና እና ሙስሊሞች የትግል ታሪክ የማይኮሩባቸውን በዘመናቸው ለሙስሊሙብጥቃት አመቻች የነበሩ ስብዕናዎችን አብዝቶ መጠቀም:
ሸኽ ሁሴን ጂብሪልን በመቻቻል ሽፋን የመቻል ትርክትን መፍጠር

🩸 ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስን "አማራ በመሆናቸው ተገለሉ" በሚል የሀሰት ትርክት ለራሱ ትግል ጋሻ ማድረግ፣ የሙፍቲውን ትግልና ማንነት መስረቅ ነው። የተከበሩትን አባባ ሸኽ ዑመርን ለዚህ ወንጀላቸው መደበቂያ ማድረግ

🩸"ወላሂ ከእንግዲህ አማራ አልሆንም" ብላ የተገደለችውን አኢሻ ሙሐመድ ደም ለመበቀል እንደሆነ መናገር፣ የቀረበው መረጃ እንደሚያሳየው ይህ ትርክት ውሸት በመሆኑ፣ ድርጊቱ የባሰ ወራዳ ይሆናል። ይህ ማለት፣ የሌለንን ሰማዕት ፈጥረው፣ በዚያ የውሸት ትርክት ላይ የራሳቸውን ፕሮፓጋንዳ እየገነቡ ነው ማለት ነው። ይህ የናዚው የፕሮፓጋንዳ ሚኒስትር ጆሴፍ ጎብልስ "ትልቅ ውሸት በተደጋጋሚ ከተነገረ እውነት ይሆናል" የሚለውን መርህ መከተል ነው።

🩸 አደም አሊ የተባለውን ግለሰብ፣ እንደተገለጸው ተራ ወንበዴና ሽፍታ ሆኖ ሳለ፣ "በስርዓቱ የተገደለብን አመራራችን" በማለት የውሸት የጀግንነት ካባ ማልበስ፣ የፕሮፓጋንዳ ማሽኑ ከምንም ተነስቶ "ሰማዕት" የመፍጠር አቅሙን ያሳያል። ይህ የውሸት ታሪክ በመፍጠር የደጋፊዎችን ስሜት ለመቀስቀስ የሚደረግ የታወቀ ስልት ነው።

🩸አንድ የፋኖ መሪ የተገደሉት ኢማም "አጎቴ ናቸው" ብሎ መግለጫ እንዲሰጥ ማድረግ፣ ወንጀሉን "የቤተሰብ ጉዳይ" ለማስመሰልና የሀዘኑን ጥልቀት ለማሳነስ የተደረገ እጅግ ርካሽ ሙከራ ነው።

ይህ "የትርክት ስርቆት" (Narrative Hijacking) ሰለባውን በድጋሚ የመግደል ያህል ነው። ህመሙን፣ ታሪኩን፣ እና ምልክቶቹን በመውሰድ አልፎ ተርፎም የውሸት ታሪክ በመፍጠር የወንጀሉን መልክ ለመቀየር መጠቀም፣ ህዝበ ሙስሊሙን ምን ያህል እንደናቁትና እንደማያከብሩት ያሳያል።



በመካነ ሰላም መስጅደ ኑር የተፈጸመውን ጭፍጨፋ ተከትሎ የፋኖ ፕሮፓጋንዳ ማሽን የተጠቀመባቸው ስልቶች፣ ድንገተኛ ወይም ያልታሰቡ ሳይሆኑ፣ በታሪክ እንደ ናዚ ጀርመን ካሉ የዘር ማጥፋት አራማጆች እና በዘመናችንም እንደ እስ$ራኤል ካሉ ወገኖች ጋር ተመሳሳይነት ያላቸውን የተፈተኑ ስልቶች በጥንቃቄ የተቀዱ ናቸው።

1️⃣ የንቀት ጥግ: ፕሮፓጋንዳው በሙሉ ህዝበ ሙስሊሙን በቀላሉ የሚታለል፣ በስሙ በሚነግዱ ጥቂት ግለሰቦች የሚወናበድ፣ የራሱን ጀግኖችና ሰማዕታት ታሪክ ከገዳዮቹ ሲሰማ እውነት ብሎ የሚቀበል የዋህ ስብስብ አድርጎ ያያል። ይህ ጥልቅ ንቀት ነው።

2️⃣ የወደፊት ጥቃት ማሳያ: አንድ ቡድን የፈጸመውን ወንጀል በዚህ ደረጃ በተደራጀ ፕሮፓጋንዳ ሲያጸድቅና የሰለባዎቹን ማንነት ሲያጠፋ፣ ለቀጣይ እና ለባሰ ወንጀል ራሱን እያዘጋጀ መሆኑን ያመለክታል። "መስጂድ ወታደራዊ ካምፕ ሊሆን ይችላል" የሚለው ትርክት ከተለመደ፣ የትኛውም መስጂድ ለጥቃት የተፈቀደ ይሆናል። "ኢማሞች ተዋጊዎች ሊሆኑ ይችላሉ" የሚለው ትርክት ከተሰረጸ፣ የትኛውም የሃይማኖት መሪ የጥቃት ዒላማ ሊሆን ይችላል።

3️⃣ የታሪካዊ ስህተት ድግግሞሽ: በታሪክ፣ እንደ ሩዋንዳው ኢንተርሃምዌ እና የቦስኒያው የሰርብ ሚሊሻዎች ያሉ ቡድኖች፣ የዘር ማጥፋት ወንጀል ከመፈጸማቸው በፊትና በወቅቱ ተጎጂዎቻቸውን "ጠላት"፣ "ከሃዲ"፣ እና "አገር አጥፊ" በማለት በፕሮፓጋንዳ ሰብዓዊነታቸውን ገፈዋል። የፋኖ ፕሮፓጋንዳም ይሄንኑ አደገኛ መንገድ እየተከተለ ነው።

በመካነ ሰላም መስጅድ የተፈጸመው አሰቃቂ ጭፍጨፋ እና እሱን ለመሸፈን የተደረገው የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ፣ ፋኖ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ያለውን ጥልቅ ንቀትና ለወደፊት ሊያደርስ የሚችለውን አደጋ በግልጽ የሚያሳይ ነው። ይህ ጉዳይ በቀላል የፖለቲካ ንትርክ የሚታለፍ ሳይሆን፣ የጦር ወንጀልን፣ የመረጃ ጦርነትን እና የጥላቻ ርዕዮተ ዓለምን አደጋዎች በአንድ ላይ የያዘ፣ ለሁሉም ትምህርት ሊሆን የሚገባ ክስተት ነው።

sheh Ali Kassa

06/10/2025

የአማራ ክልል ካለበት ውጥንቅጥ ለማውጣት ምን እናድርግ?

በመካነ ሰላም ኑር መስጂድ ውስጥ የነበሩ የመጅሊስ ምክትል ሰብሳቢ ኢማም ፣ የመስጂድ ጥበቃ እና ሙአዚን ላይ የተኩስ እሩምታ የከፈተ አካል «ጉዳዩ ሀይማኖታዊ ቅርፅ የለውም!» ብሎ ሲሟገት ምላሽ የመስጠት «አፕታይቱ» የለኝም። ይልቁኑ አንድ አጀንዳ ላይ ደጋግሞ በመጣበቅ እውነታን ለመሸፈን መሞከሩን ትተን የአማራ ክልል ከሁሉም ጎረቤቶቹ ጋር ጠላት ያደረገውን አካሄድ ቆም ብለን እናስብበት እላለው።

በዚህ ጊዜ ክልሉ ውስጥ እየተፈጠረ ያለውን ካስተዋልን ፤ በሰሜን ከትግራይ አይን እና ናጫ ሆኗል። በጎኑ ከሱዳን ጋር አልፎ አልፎ ቦግ እያለ የሚቀዘቅዝ ፍልሚያ አለበት። በደቡብ ከኦሮሚያ ክልል ጋር የማይቀር ግብግብ ውስጥ ተነክሯል። ይሄ ሁሉ ጠላት ያካበበው መሆኑ ሳይበቃ በስመ «ፋኖ» የተደራጀው ቡድን ቀንበቀን አዳዲስ ጦርነት እየሳበ ወደ ክልሉ ማዝቁን ግን የማቋረጥ ፍላጎቱ ያለው አይመስልም።

🪖 የጎንደር ፋኖ ከጎጃም ፋኖ ይዋጋል

🪖 የጎጃሙ ከወሎ ጋር ሰላም የለውም

🪖 የሸዋ ፋኖ እንዲሁ ከሌሎቹ የፋኖ እንቅስቃሴዎች ጋር ፍፁማዊ አለመስማማት አለው።

🪖ሁሉም ፋኖዎች ደግሞ ከፌዴራል መንግስቱ ጋር ጠበኛ ናቸው።

🪖እንደህዝብ የአማራ ክልል ነዋሪ ፤ መከራን ቁርስና ምሳ ያደረጉበትን «ዱር አደሮች» የመገላገል ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያየለ መጥቷል።

🪖ይሄ ሁሉ ግብግብ ሳይበቃ የሞአ ተዋህዶ እጆች የአማራን ትግል ጠልፈው ሀይማኖታዊ ሽፋን አልብሰውታል።

ይሄ አካሄድ ጥቅሙ ለየትኛው የማህበረሰብ ክፍል ነው? ስንል እንጠይቃለን። እውን የፋኖ ንቅናቄ የአማራ ክልል አንድነት አመጣ ወይስ ልዩነቱን አሰፋው? በክልሉ የተፈጠረውን አለመረጋጋት አባባሰው ወይስ ቀነሰው? ክልሉ በሀይማኖት የነበረውን የመደማመጥ ባህል አዳበረለት ወይስ ወደባሰ አዘቅት ውስጥ ጨመረው? …

ከሁሉ አንፃር ብንመለከተው በፋኖ ፅንፈኛ አካሄድ የተጠቀመው «ዱር አደሩ» ሽፍታ ብቻ ነው። ባሰኘው ሰአት እየዘረፈ እና እየገደለ ያለተጠያቂነት ኑሮውን ይገፋል። ከዚህ በተረፈ ግን ሀገሪቱም ሆነች ክልሉ ለዘመናት ያፈሩትን ንብረት ከማወረደም የዘለለ ጠብ ያለ መፍትሄ አላገኙም። ችግሩን እንዲህ በግልፍተኛነት እና ፅንፍ በረገጡ እሳቤዎች ለማረጋጋት መሞከር እሳትን በቤንዚል ለማጥፋት እንደመሞከር ሆኖ ነው የሚታየኝ። ስለዚህ የአማራ ክልል ምሁራን እና አሳቢዎች ነገሮች ከዚህ በላይ መልክ ከማጣቸው አስቀድመው ሊነቁ ይገባቸዋል።

እንደግል ግን ለክልሉ ችግር መፍትሄ ይሆናሉ ብዬ የማስባቸውን ሶስት መሰረታዊ ሀሳብ አንስቼ መጣጥፌን ልቋጭላቹ

1️⃣ ፖለቲካ እና ሀይማኖትን መለየት፦ በተለይም በፋኖ አደረጃጀት ላይ እየተርመሰመሰ ያለውን የ«ሞአ ተዋህዶ» እንቅስቃሴ በጋራ መታገል አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው። አማራነትን በአዲስ መገለጫ ለመሳል እና ከውጫዊ ችግሮቹ ይልቅ በውስጣዊ ትግል እንዲባክን እያደረገ ያለውን አካል እጅ ሳይዙ ለትግል መንቀሳቀስ ክልሉን ለተራዘመ ስቃይ ከመዳረግ የተዘለለ መፍትሄ አያመጣም። ስለዚህ አማራነትን ሁሉን አቀፍ ወደሆነ መገለጫ አሳድጎ ያለጎጥ እና ሀይማኖታዊ ልዩነት በመሰባሰብ ሀይልን ማጠናከር ያስፈልጋል።

2️⃣ ለድርድር ዝግጁ መሆን፦ በክልሉ እየተካሄደ ያለውን የ«እንካ ቅመስ» ፖለቲካ ሊያበርድ የሚችለው ሌላኛው መፍትሄ የድርድር አቅም መፍጠር ነው። የትኛውም የአለማችን ክፍል ላይ የሚደረጉ ፍልሚያዎች ጎንለጎን ትግላቸውን የሚያካሂዱበት ጠንካራ መሳሪያ ፖለቲካዊ ድርድር መሆኑ አይታበልም። ለዚህ ደግሞ በማናለብኝነት ክልሉ ላይ እየፈነጨ ያለውን መሳሪያ ታጣቂ ስርአት ማስተማር እና የሰላም አቅጣጫን ማሳየት ይፈልጋል። ከክልላዊ እይታ ከፍ ብሎ በአለም አቀፍ ደረጃ ፖለቲካ የሚከተለውን አቅጣጫ ማንበብም ግድ ይላል። ወደድንም ጠላን የፌዴራል መንግስት በአለም አቀፍ ደረጃ የሀገሪቱ ገዥ መሆኑ አይቀርምና በብልጠት ተደራድሮ ሙሉ እንኳ ባይሆን ከፊል ፍላጎቶችን ማስፈፀም አራድነት ነው።

3️⃣ተጨማሪ ቁርሾዎችን ማስቀረት፦ በክልሉ የረዥም ጊዜ ታሪክ አንፃር ከውጫዊ ትግል በተጨማሪ ውስጣዊ ፍትጊያዎች መፈጠራቸው አያጠያይቅም። ሆኖም የውስጥ ፍትጊያዎች በበዙ ቁጥር ትግሉ ቀርቶ እንደህዝብ አንድነትን አስጠብቆ የመቆየት ጉዳይ እንኳ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ይወድቃልና የእስካሁኑ ቁርሾዎች እንዳሉ ሆነው አዲስ ቁርሾ የሚወልዱ ሀሳቦችን መጠንቀቅ ያስፈልጋል። ለምሳሌ፦ የግእዝ ቋንቋን በግዳጅ የማጥበቅ አካሄድ ፤ በፀሎት ቦታዎች ላይ የሚከሰቱ ጥቃቶች ፤ አማራነትን በሀይማኖት የመግለፅ አካሄዶች… ቅድሚያ ተሰጥቶ የመፍትሄ አቅጠሰጫ ሊበጅላቸው ይገባል። አለዚያ ግን ክልሉም ከአንድ ችግር ወደ ባሰው እያዘገመ ፤ ህዝቡም ከነበረበት መከራ ወደ ባሰው እየተዘፈቀ የመዳን ተስፋው እንዳይጨልም ያሰጋል።

የግዕዝ ትምህርት ተቃውሞ ገጠመውየአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የቋንቋ እና ሥነ ጽሑፍ መምህር የሆኑት ዶክተር በድሉ ዋቅጅራ የግእዝ ትምህርት በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መስጠቱ እርባና የለውም ...
15/09/2025

የግዕዝ ትምህርት ተቃውሞ ገጠመው

የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የቋንቋ እና ሥነ ጽሑፍ መምህር የሆኑት ዶክተር በድሉ ዋቅጅራ የግእዝ ትምህርት በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መስጠቱ እርባና የለውም ሲሉ ከቢቢሲ አማርኛ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገለፁ !

"ግእዝ የሞተ ቋንቋ ነው" የሚሉት መምህር በድሉ፣ ይህንን ቋንቋ እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት ከሦስተኛ ክፍል ጀምሮ መስጠቱ እርባና የለውም ብለዋል።

አንድ ቋንቋ የአፍ መፍቻ ተናጋሪ ከሌለው እና ከ25 ሺህ በታች ተናጋሪ ካለው ሞቷል እንደሚባል የሚናገሩት መምህሩ፣ ይህንን "የሞተ ቋንቋ" ከታች ከፍል ጀምሮ መስጠት የተማሪዎችን ጊዜ ማጥፋት እንደሆነ ገልጸዋል።

ቋንቋን የመማር ወሳኝ ዓላማ ለተግባቦት እና ሕይወትን ለመምራት እንደሆነ የሚናገሩት መምህር በድሉ ግእዝ ለተግባቦትም ሆነ ሕይወትን ለመምራት አሁን ላይ ጥቅም የለውም ብለዋል።

ሆኖም የግእዝ ቋንቋ ጭራሽኑ በትምህርት መልክ መሰጠት የለበትም የሚል አቋም የላቸውም።
የግእዝ ቋንቋ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ በጀርመን እና በፈረንሳይ ውስጥ ይሰጣል የሚሉት መምህር በድሉ፣ ቋንቋው የሚሰጠው በግእዝ ቋንቋ ምርምር ማድረግ ለሚፈልጉ ብቻ መሆኑን ይጠቅሳሉ።
በመሆኑም ትምህርቱ ይሰጥ ከተባለም መሰጠት ያለበት ከ9 ክፍል ጀምሮ ወይም ለአንትሮፖሎጂ፣ ለታሪክ እና ለቋንቋ ጥናት ፍላጎት ላላቸው የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች እንዲሆን መምህሩ ይመክራሉ።

ዩኒቨርሲቲ ከገቡ በኋላ ለአንድ ዓመት የግእዝ ቋንቋ መማራቸውን የሚናገሩት መምህር በድሉ፣ ግእዝ አይጠቅምም የሚል አቋም ባይኖራቸውም፤ የተግባቦት እና የሕይወት ጥቅሙ ውስን የሆነን ቋንቋ ከሦስተኛ ክፍል ጀምሮ መስጠት "ለተማሪዎች የጊዜ ብክነት ነው የሚሆነው" ሲሉ ውሳኔውን ተችተዋል።
"ተማሪዎቹስ ዘጠኝ ዓመት ሙሉ ምንድን ነው የሚማሩት?" ሲሉም በሚኖረው ዝግጅት ላይም ጥያቄ አንስተዋል።

የግእዝ ቋንቋ ትምህርት በሙሉ ትግበራ ከሦስተኛ ክፍል ጀምሮ መሰጠት የተጀመረው ባለፈው ዓመት ቢሆንም በመምህራን እጥረት ምክንያት በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ማዳረስ ሳይቻል መቅረቱን ክልሉ ለቢቢሲ መግለጹ አይዘነጋም።

(ቢቢሲ አማርኛ)

03/09/2025

መለስ የአባይ ግድብን ባያስጀምረው ኖሮ አብይ ግድብ የሚባል ፕሮጀክት ሀሳቡም አይመጣለትም ነበር!

Late PM Meles Zenawi is the father of GERD (Abay Dam)!የቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ የአባይ ግድብ አባት ነው!ከነአምባገነንነቱ አባይ ግን የእርሱ ውለታ ነው!
03/09/2025

Late PM Meles Zenawi is the father of GERD (Abay Dam)!
የቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ የአባይ ግድብ አባት ነው!
ከነአምባገነንነቱ አባይ ግን የእርሱ ውለታ ነው!

Address

Congo Street
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የኢትዮጵያውያን ድምጽ - Ethiopian Voice posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የኢትዮጵያውያን ድምጽ - Ethiopian Voice:

Share