ስፖርት መሀል ሸገር አራዳ Sport Mehal Sheger Arada

ስፖርት መሀል ሸገር አራዳ  Sport  Mehal Sheger Arada ስፖርት ለሁለንተናዊ ዕድገት!

19/02/2025
19/02/2025

የካቲት ፲፪ የሰማዕታት ቀን!!

ፋሽስት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ ላይ ለፈጸመው ጭፍጨፋና ዝርፊያ የኢጣሊያ መንግሥት ይቅርታ ሊጠይቅና ካሣ ሊከፍል ይገባዋል!!

የዛሬው ዕለት የካቲት ፲፪ ቀን (የሰማዕታት ቀን) በኢትዮጵያ በታሪክ የፋሽስቶች ዘረኝነት፣ አውሬያዊ ጭካኔና አረመኔነት በገሃድ የታየበት ቀን ነበር፡፡

በወቅቱ ፋሽሽት በኢትዮጵ ሕዝብ ሕዝብ ላይ ያደረሰውን እጅግ አረመኔያዊ የኾነ ጭካኔና እልቂት በተመለከተ የውጪ ሀገራት ጋዜጠኞችና ታዛቢዎች ከተዉልን የታሪክ ማስታወሻ ጥቂት ሰበዞችን እንምዘዝ እስቲ፤

በወቅቱ በአዲስ አበባ የነበረ አንድ አውሮፓዊ ሐኪም እለቱን እንዲህ ነበር የገለጸው፤

‘‘… ምን ዓይነት አጨካከን ነው፣ ደም በመንገድ ላይ እንደ ውኃ ሲፈስ ያየኹት የዚያን ጊዜ ነው፡፡ የወንዶች፣ የሴቶች፣ የልጆች ሬሳ በያለበት ተኝቷል፡፡ ወዲያው ከባድ የቃጠሎ ጭስ አዲስ አበባን ፅልመት አለበሳት፡፡ የኗሪዎች ቤት ከተፈሸ በኋላ ሰዎቹ በውስጥ እንዳሉ እሳት ተለቀቀባቸው፡፡ ቃጠሎው ቶሎ እንዲያያዝም ቤኒዚንና ዘይት ይጠቀሙ ነበር፡፡ ሰው እሳቱን እየሸሸ ከቤቱ ሲወጣ በመትረየረስ እሩምታ ይገድሉታል፡፡

በዓለም ጦርነት ጊዜ ቁስለኛ ለማንሳት ከግንባር ከቀደመው ጦር ጋር አምቡላንስ ውስጥ እሠራ ነበር፡፡ በሌላም ጦርነቶች ውስጥ ተካፋይ ኾኛለኹ፡፡ በሕይወቴ እንደ አዲስ አበባ ያለ እልቂት ግን አላየሁም፡፡’"

የፋሽስቱ ቤኒቶ ሞሶሎኒ ተወካይ ሩዶልፎ ግራዚያኒ በሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ላይ የወሰደውን ርምጃ አስመልክቶ በሮማ ላለው ቅኝ ግዛት ሚ/ር መስሪያ ቤት በቁጥር 14-1154 ባስተላለፈው የቴሌግራም መልእክት እንዲህ ነበር ያለው፤

‘‘እነኚህ ጥቁሮች [ኢትዮጵያውያን] የኛን ወታደር ሲያዩ፤ ‹‹ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር! ይላሉ፡፡ ይህን የሚሉትም ለመቀጣጫ እንዲሆኑ ሁሉንም አስጨርስኳቸው፤›› ብሏል፡፡

በዚያው ዘመን እ.ኤ.አ. በየካቲት 22 ቀን የወጣው የሮም ጋዜጣ "ዴል ፖፖሎ"፤ "የአዲስ አበባ አጋማሽ በአሰሳው ጸድቷል፣ 2000 ኢትዮጵያውያን ተይዘው ወደ ደናኔና ወደ ሌሎች ማሰሪያ ቦታዎች ተልከዋል፡፡’" ሲል ዘግቦ ነበር፡፡

ፋሽስቱ ቤኒቶ ሞሶሊኒ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የነበረውን ንቀትና ጥላቻ ያሳየበትና ቢቻለውም ቤተ ክርስቲያኒቱን በፋሽስት ወይም በሮማ አስተዳደር ሥር እንድትሆን የነበረውን ሕልም የሚያጋልጠው እ.ኤ.አ. ታኅሣሥ 16/1935 በአስመራ ለሚገኘው ለጦር አዝማቹ ለማርሻል ባዶሊዮ ያስተላለፈው ጥብቅ ምሥጢራዊ ቴሌግራም እንዲህ ይነበባል፡-

በቁጥር 421M እና በቁጥር 426 ዳግም ያስተላለፍክልኝን የምስጢር ቴሌግራም ደርሶኝ በሚገባ አይቼዋለሁ፡፡ የአክሱም ገዳም ተቀደሰ ሥፍራ እንደመሆኑና ካለውም ጥንታዊ ታሪክና ቅርስ አኳያ በጦር መሣሪያም ሆነ በማናቸውም ዓይነት ወረራ እንዳይነካና የኢትዮጵያዊነቱን እንደያዘ መቆየት አለበት የሚለውን የውጭ መንግሥታት አሳብ ከምንም አልቆጥረውም ማለትህና ወደፊትም ይህን አሳብ የምቀበል ሰው አይደለሁኝም ማለትህ ትክክለኛ ነህ፤ ጥሩም አድርገኻል፡፡

በተመሳሳይም አውሮፓዊው ጋዜጠኛው ቺሮ ፖጃሊ ፋሽስቶች የካቲት 13 ቀን 1929 ዓ.ም. በአራዳ ጊዮርጊስ ቤ/ክ ያደረጉትን ጭፍጨፋና ግፍ እንዲህ ዘግቦት ነበር፡፡

"ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ ውስጥ ሰዎች መደበቃቸው ስለተሰማ ቤተክርስቲያኑ ውስጥ ቤኒዚን ተርከፍክፎ እሳት ተለቀቀበት፡፡ የቤተክርስቲያኑ ንዋያተ ቅድሳት፤ መጻሕፍትና ሥዕሎች በአጠቃላይ በእሳት ነደዱ፡፡ ከቤተክርስቲያኑ ውስጥ ከእሳቱ ለመሸሽ 50 ያህል ሰዎች ሲወጡ ተያዙና ከቤተክርስቲያኑ ጓሮ ተወስደው በቦምብ እንዲገደሉ ተደረገ፡፡"

የኢትዮጵያ ታላቅ ባለውለታ የነበሩትና የኢጣሊያን ፋሽስት ጭካኔና ግፍ ለዓለም ሁሉ በማጋለጥ ከኢትዮጵያውያን ጎን የቆሙት ሲሊቪያ ፓንክረስት- የፋሽስቱ መሪ ቤኒቶ ሞሶሊኒ በሃይማኖት አባቶች ላይ እየተወሰደ ያለው ርምጃ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን ሊያሸማቅቅ እንደሚችልና ጭፍጨፋውም ውጤታማ እንደሆነ በወቅቱ ለምስራቅ አፍሪካ ለቅኝ ግዛት ሚ/ሩ ለግራዚያኒ ያስተላለፈውን ምስጢራዊ የቴሌግራም መልእክት ‹Ethiopia and Eritrea› በሚለው መጽሐፋቸው እንዲህ ጠቅሰውታል፡-

… The ex*****on of Abune Petros, one of the four Ethiopian bishops, has terrified the leaders and the public. The work of repression against armed groups dispersed in the forest continues. All prisoners have been shot. Inexorable reprisals have been effected against the populations guilty, if not complicity, at least of lack of favorable attitude. (A telegram of March 1, 1937)

ትርጉም፡- ‹‹በአቡነ ጴጥሮስ ላይ የተወሰደው የግድያ ርምጃ ብዙዎችን እንዲፈሩና እንዲሸማቀቁ አድርጓል፤ ይህ ዓይነቱ ርምጃ ለኢጣሊያን እንዳይገዛ ሕዝቡን በሚያነሣሡና በዱር በገደል በአርበኝነት በተሰማሩት ፋኖዎችም ላይ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባዋል…፤››

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ በፋሽስት ለደረሰባት ግፍ፣ ጭፍጨፋ፣ ዝርፊያ… የኢጣሊያ መንግሥት ይቅርታ ሊጠይቅና ካሣ ሊከፍል ይገባዋል!!

ክብር ለኢትዮጵያ ነጻነት ሲሉ በግፍ ለተጨፈጨፉ ሰማዕታት!!

(Dn. Terefe W.)

18/04/2024
26/07/2023

ትግራይ መቀለ ነው ። ከከተማ አስተዳደሩ ፊት ለፊት ያለ አቧራማ ሜዳ ! ዕነዚህ ዕድሜያቸው ከ13-15 ያልበለጡ ታዳጊዎች የሚያቃጥለው ፀሐይ ደንታ አልሰጣቸውም ። ዐይን የሚያጠፋው አቧራም ግዳቸው አይደለም ። ከቤት በጠዋት ከወጡ ሰዓታት ተቆጥረዋል ።

ማታ ሲመሽ ነው የምንገባው አለኝ አንደኛው ልጅ ...

ና ግባ ተጫወት መሃል ባልገባ ወይስ ምን ይሻልሃል አለኝ ? የሳሳች ካፖርተኒ ኳሷን እያነጠረ !

ኸረ ጋሼ ዋ ልብስህ ይቆሽሻል አለ አንዱ ተከትሎ በአክብሮት ! ገረመኝ ። ልጅነቴ ታወሰኝ ። የጨፌ ቆርቆሮ ሜዳ አቧራማ ሜዳዎች ፈረንሳይ ለጋሲዬን ! እግር ኳስ የትም በምንም ማህበራዊ ቀውስ ውስጥ በፍቅር የሚተገበረው ዓለምን ያስተሳሰረው ተወዳጅ ጨዋታ ነው ።

በዕነዚህ ታዳጊዎች በደስታ ሕጉ ተጠብቆ ይተገበራል ።

የባርሴሎና አርሰናል ዩናይትድ የተቀዳደዱ መለያዎችን ለብሰዋል ። የእግሮቻቸው ዓውራ ጣቶቻቸው ምቹ ባልሆነው ሜዳ ክፉኛ ተጎድተው ከባዶ እግር ያልተናነሱ ጫማዎች ተጫምተው እግር ኳስን በፍቅር ይጫወታሉ ። ህልማቸው እንደ ሳላዲን ሰይድ አዳነ ግርማ አማኑዔል ገብረ ሚካዔል ሽመልስ በቀለ ጌታነህ ከበደ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን መጫወት ነው ።

ስፖርት በትግራይ ስሜት ነው ። በፍላጎት በፍቅር በምንም የህይወት ፈተና ውስጥ ይተገበራል ። በጦርነቱ ሰዓት አንጫወትም ነበር ። አሁን ግን እየተጫወትን ነው አለኝ አንደኛው ታዳጊ አቧራ የቃመ ፊቱን እየጠራረገ ! አንተ ሌላ ካለህ ሸራ ጫማህን ትሰጠኛለህ አለኝ ። ቀጠለናም ኳስም የለንም ብትገዛልን ደስ ይለናል አለ ትግሬኛ አማረኛ በቀላቀለ ደስ የሚል ቅላፄ !

ከስንብቴ በፊት የዕነዚህ ልጆች የመጨረሻ ቃል ነው ።

ዘር ሀይማኖት ብሄር ፖለቲካ የማይሻው ስፖርት በትግራይ ከጦርነቱ ማግስት ሰፊ ማህበራዊ ቀውስ በፈተነው ክልል ቅንጦት ቢመስልም ገብቶን ከተጠቀምንበት ግን ሀያል አቅም አለው ። ስፖርት ድንብር ተሻጋሪ ዓለምን ያስተሳሰረ ተፅእኖ ፈጣሪ ነው ። የተጣሉትን ያስታረቀ የጦፈ ጦርነት ያስቆመ ማህበራዊ ትስስርን ከፍ ያደረገ የሰላም መሣሪያ ነው ።

መቀመጫቸውን በትግራይ አድርገው የክልሉ ዋና የእግር ኳስ ቀለም በመሆን ሀገራቸው ኢትዮጵያን በኢንተርናሽናል መድረክ የወከሉ ኮኮቦችን ያፈሩ ከተደራጀ ህዝባዊ መሠረት ጋር በኢትዮጵያ እግር ኳስ ተደናቂ የፍክክር መንፈስ ይዘው ይንቀሳቀሱ የነበሩት መቀለ 70 እንደርታ ወልዋሎ አዲግራት ስኹል ሽረ የመሣሠሉ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ዛሬ ሊፈርሱ ገደል አፋፍ ቆመዋል ።

ከጦርነቱ ማግስት ከዓመታት በፊት በሚሊየን የሚከፈላቸው የክለቦቹ አንዳንዶቹ ተጨዋቾች በህይወት በልቶ አድሮ ለመኖር መቀለ ሰኞ ገቢያ የቀን ስራ ተባረው እየሰሩ ይገኛሉ ። ወትሮም እንኳን ዘንቦብሽ በሆነው የኢትዮጵያ ስፖርት እንቅስቃሴ ስፖርት በትግራይ አሁን በህልውና የመቀጠል ጉዳይ ሆኗል ።

በባዶ እግር እነዛ በጠራራ ፀሐይ አቧራ እየቃሙ እግር ኳስን በነፃነት በፍቅር የሚጫወቱ የትግራይ ታዳጊዎች መቀለን ጨምሮ በክልሉ የተለያዩ ከተሞች ታወሱኝ ? የህይወት ዕጣፈንታ የሌት ተቀን ፈተናቸው ከእራሴ አወዛገበኝ ።

የሰላም ዋጋው ስንት ይሆን ? ብቻ እግር ኳስ ስፖርት በትግራይ ከቀውሱ ማግስትም በፈራረሱ መሠረተ ልማቶች መሃል በፍቅር ይተገበራል ። ህፃናት ታዳጊዎች በመቀለ ከከተማ አሰተዳደሩ ህንፃ ፊት ለፊት ባለ አቧራማ ሜዳ ጨምሮ ከፕላኔት ሆቴል ፊት ለፊት ስቴዲየሙ ጎን ሌት ተቀን ኳስን ተቧድነው ሲጫወቱ አየሁ ።

ወደ ትግራይ አቅንተው ፕላኔት ሆቴል መቀለ ካረፉ የዕነዚህ ታዳጊዎች በጩኸት የታጀበ የኳስ ጨዋታ ድባብ ከእንቅልፎዎ በጠዋት ሊቀሰቅስዎ ይችላል ።

ሊከስሙ የተቃረቡ የትግራይ ክልል አውራ ክለቦችን መልሶ በማቋቋም እነዛ ታዳጊዎች የነገ የእነርሱ ባልሆነ ሃጢያት የተፈተነ የህይወት ተስፋን ማለምለም ታሪክም የህይወት ዘላዓለማዊ ስንቅ ንሰሀም ነው ።

እናም ውድ ወገኖች በትግራይ ክልል ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ከፍ ያለ መነቃቃት የሚፈጥረው ''ክለቦቻችንን እንታደግ የተሰኘው ታላቅ ማህበራዊ ግብ የሰነቀ ጥሪን በመቀላቀል ሊጠፉ የተቃረቡ ክለቦችን መታደግ ? በበርካታ ማህበራዊ ቀውሶች ውስጥም ሆነው እግር ኳስን በእነዛ ያልተመቸ አቧራማ ሜዳ በፍቅር የሚጫወቱ ነገ እንደ ሳላዲን ሰይድ በዋልያው መለያ ለእናት ሀገራቸው ኢትዮጵያ መጫወት የሚመኙ የትግራይ እልፍ ታዳጊዎችን ህልም ማለምለም ከተዳፈነው ድቅድቅ የህይወት ጨለማም ማውጣት ትውልድ ዛሬም ነገም የሚዘክረው ሀገራዊ የኢትዮጲያዊነት አደራም ነው ።

እናም ውድ በሀገር ቤትም ሆነ በመላው ዓለም የምትገኙ ኢትዮጲያዊያን በቀጣይ ቀናት በመገናኛ ብዙሃን በማህበራዊ ሚዲያው ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ውበት ጌጥ የነበሩ የትግራይ ክልል ክለቦችን መልሶ ሟቋቋም ከመፍረስ ለማዳን
'' ክለቦቻችን እንታደግ "በሚል መሪ ቃል የተጀመረውን የተደራጀ ማህበራዊ ሚናን ከግቡ ለማድረስ ይፋ የምናደርጋቸው የዘመቻው ፓኬጆችን በመደገፍ ስፖርት ከዘር ከብሄር ከፖለቲካ ከሀይማኖት በፀዳ መልኩ በማረጋገጥ ዘመን የማይረሳው ትውልድ የሚዘክረው ሕያው ታሪክ እንድንሰራ በአክብሮት ጥሪዬን አስተላልፋለሁ ።

ምክንያቱም አርሰናል ዩናይትድ ሲቲ ሊቨርፑል ወይ ቼልሲ ማድሪድ ባርሳ እያልን የምንወዳቸው ክለቦች ሌት ተቀንም የምንደግፋቸው እንደ ስሜታችን እንደ ጨዋታ እንቅስቃሴ ውበታቸው የህይወት መዝናኛችን የሆኑ የእግር ኳስ ክለቦች ስለሆኑ እንጂ በብሄራቸው ወይ ፖለቲካዊ አቋማቸው መርጠን አይደለም ። የመቀለ 70 እንደርታ ወልዋሎ ሽረ እና ሌሎች የትግራይ ክለቦች ወቅታዊ ነበራዊ ሐቅም ይህ ነው ።

'' ክለቦቻችንን እንታደግ "
ስፖርት ለሰላም ስፖርት ለሀገር አንድነት --
ኤፍሬም የማነ

05/06/2023

ለሁሉም የስፖርት ሚዲያዎች

የሚዲያ ሽፋን ጥያቄን ይመለከታል

የአፍሪካ ዞን 4 የጎልፍ ስፖርት ሻምፒዮና ውድድር በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ከግንቦት 28 - ሰኔ 04/2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል ።

በመሆኑም የወድድሩ መክፈቻ ነገ ማክሰኞ ግንቦት 29/2015 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ጦር ኃይሎች በሚገኘው ጎልፍ ክለብ በመሆኑ በዕለቱና በሰዓቱ በቦታው በመገኘት መረጃውን ለህዝብ እንድታደረሱ የኢትዮጵያ ጎልፍ አሶሴሽን ጥሪውን ያስተላልፋል ።

01/06/2023
29/05/2023
29/05/2023
ሁለት ገፅታ ያላት ሀገር … ኢትዮጵያ
29/05/2023

ሁለት ገፅታ ያላት ሀገር … ኢትዮጵያ

ከኳስ ዓይነቶች ስንቱን ያውቃሉ?1.እግር ኳስ    2. ?    3. ?   4.? . ? …………….የተሻለ ላወቀ የሞባይል ካርድ!
24/05/2023

ከኳስ ዓይነቶች ስንቱን ያውቃሉ?
1.እግር ኳስ 2. ? 3. ? 4.? . ? …………….
የተሻለ ላወቀ የሞባይል ካርድ!

24/05/2023

Manchester City has WON the League but WON our hearts! 💕

We Are The Gunners👌👌👌

Address

Addis Ababa

Telephone

+251912241130

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ስፖርት መሀል ሸገር አራዳ Sport Mehal Sheger Arada posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ስፖርት መሀል ሸገር አራዳ Sport Mehal Sheger Arada:

Share