Goh Bedembia Charitable Association

Goh Bedembia Charitable Association Goh Be Dembia Charitable Association

ሰውዬውን በሀገር ባህል ልብስ ስራው እናውቀዋለን: በቅርቡም በሪል እስቴትና አፖርታማ ዘርፍ ላይ ተሰማርቷል።ለበጎነት ሁሌም ከፊት ይገኛል!! ለአብነትም:-* ማህበራዊ ሚዲያን ተጠቅሞ እርዳታ ...
02/08/2023

ሰውዬውን በሀገር ባህል ልብስ ስራው እናውቀዋለን: በቅርቡም በሪል እስቴትና አፖርታማ ዘርፍ ላይ ተሰማርቷል።

ለበጎነት ሁሌም ከፊት ይገኛል!! ለአብነትም:-

* ማህበራዊ ሚዲያን ተጠቅሞ እርዳታ የሚሹ ወገኖችን post በማድረግ ተማጽኖ ያስተጋባል: ሲያሻው ገንዘብ ይሰጣል: ሰላምን ይሰብካል: አፋልጉኝ ይላል: መመስገን ያለበትንም ሲያመሰግን ተመልክተናል (ምስክሮችም ነን!!): ሲሰጥ እምነት 'አይገደውም': የቻለውን ሲያደርግ እና ሰው ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው በማለት ሁሌ አለኝታውን ያሳያል።

ሙስጠፋ መስዑድ // 5,000.00 ብር

አሁንም አለኝታነትህን እንደተለመደው ስላሳየኸን ፈጣሪ አብዝቶ ይስጥህ እንላለን። እናመሰግንሃለን።❤❤❤

ማህበራችንን መርዳት ለምትፈልጉ

የጎህ በደምቢያ የበጎ አድራጎት ማህበር ሂሳብ ቁጥር

ኢትዮጺያ ንግድ ባንክ 1000491543136
አቢሲንያ ባንክ 61620947
ስለምታደርጉልን ቀናኢነት አብዝተን እናመሰግናለን//

ወገኑንና ሀገሩን አብዝቶ የሚወደው ለተጠየቀው ድጋፍ ሁሉ ሳይሰስት በደግነት እጁን የሚዘረጋው ወንድማችን ግዛቸው አጣናው ከአሜሪካ እኛ እያለን መቼም ተማሪ የሆኑ እህት ወንድሞቻችን በአቅም ማ...
29/07/2023

ወገኑንና ሀገሩን አብዝቶ የሚወደው ለተጠየቀው ድጋፍ ሁሉ ሳይሰስት በደግነት እጁን የሚዘረጋው ወንድማችን ግዛቸው አጣናው ከአሜሪካ እኛ እያለን መቼም ተማሪ የሆኑ እህት ወንድሞቻችን በአቅም ማነስ የተነሳ ት/ት ማቋረጥ የለባቸውም በማለት 15,000.00 ብር ለማህበራችን ገቢ አድርጎልናል።

ግዝሽ ሁሌም ከጎናችን ስለሆንክ እናመሰግንሃለን 🙏🙏

ወንድማችን ጌታነህ ተካ የላከልንን እንዲሁ አቅርበንላችኋል። * ከ1ኛ - 8ኛ ክፍል ስማር ደብተር የገዛሁት ለአንደኛ ክፍል ብቻ ነበር ከ2ኛ ክፍል ጀምሮ ከነመመዝገቢያየ ሙሉ ደብተር አትረፍር...
20/07/2023

ወንድማችን ጌታነህ ተካ የላከልንን እንዲሁ አቅርበንላችኋል።

* ከ1ኛ - 8ኛ ክፍል ስማር ደብተር የገዛሁት ለአንደኛ ክፍል ብቻ ነበር ከ2ኛ ክፍል ጀምሮ ከነመመዝገቢያየ ሙሉ ደብተር አትረፍርፈው የሚገዙልኝ የቆላድባ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ሰራተኞች ነበሩ!!

* ይህቺ ትንሽየ መዋጮ ብታንስም ከ1995 እስከ 2002 እያበላችሁ እያጠጣችሁ እያከማችሁ እያሳከማችሁ ላስተማራችሁኝ ከጥበቃ እስከ ሀላፊነት ቦታ የነበራችሁ መላ የተቋሙ ሰራተኞች ስም ይሁንልኝ: ይላል።

እኛም እናመሰግንሃለን ጌትዬ ምክንያቱም የአብዛኞቻችን ተማሪዎች ታሪክ ከዚህ የተለየ አይደለምና//

ብርቱ: ሀገር ወዳድ: በሁሉም ዘርፍ እኔ አለሁ ባይ ወንድማችን ሰጠኝ ገብሩ ከሀገረ አሜሪካ 10,000.00 ብር ሰጠኝ ሰጥቶናል። እግዚአብሔር ያክብርልን እንደሰጠህን ይስጥህ: እናመሰግናለን።...
19/07/2023

ብርቱ: ሀገር ወዳድ: በሁሉም ዘርፍ እኔ አለሁ ባይ ወንድማችን ሰጠኝ ገብሩ ከሀገረ አሜሪካ 10,000.00 ብር ሰጠኝ ሰጥቶናል።

እግዚአብሔር ያክብርልን እንደሰጠህን ይስጥህ: እናመሰግናለን።🙏🙏🙏

ደግነት የማይበሰብስ ብቸኛ ልብስ ነው!!ትላንት ከጎናችን ነበራችሁ ዛሬም አብራችሁን እንደምትሆኑ እያመን በ3ኛው ዙር ልጆችን ወደ ት/ት ቤት እንዲሄዱ እናድርግ፡፡ ባሳለፍንባቸው 2 የበጎነት ...
18/07/2023

ደግነት የማይበሰብስ ብቸኛ ልብስ ነው!!

ትላንት ከጎናችን ነበራችሁ ዛሬም አብራችሁን እንደምትሆኑ እያመን በ3ኛው ዙር ልጆችን ወደ ት/ት ቤት እንዲሄዱ እናድርግ፡፡

ባሳለፍንባቸው 2 የበጎነት አመታት፡-

 787 ደርዘን ደብተርና እስክርቢቶ እንዲሁም አጋዥ መጽሐፍትን በቆላድባ ከተማ አስተዳደር ላሉና ጥቂት በወረዳው ለሚገኙ ችግረኛ ተማሪዎች በየቀበሌው ለማበርከት ተሞክሯል߹

 ለደምቢያ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የተለያዩ የህክምና ቁሳቁሶችን አበርክተናል߹

 ጤና መድህን ላይም አጋርነታችንን አሳይተናል߹

 እርዳታችንን ለሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎች ተሰማርተን ቆይተናል፡፡ አጠናክረንም የምንቀጽል ይሆናል߹

 በቀጣይ በትምህርት ሴክተርና በቆላድባ ከተማ ለሚገኙ "ምስኪኖች" የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል አቅደን ተነስተናል፡፡

ስለሆነም በዚህ አመት ማህበራችሁ፡ ማህበራችን እንደ ከዚህ ቀደሙ ለችግረኛ ተማሪዎች የትምህርት ቤት ቁሳቁሶችን እና ለሴት እህቶቻችን ያለባቸውን የንጽህና መጠበቂያ (ሞዴስ) ችግር ለመቅረፍ በመረባረብ ላይ እንገኛለን፡፡

ስለሆነም ይህንን ህጋዊ ማህበር በማገዝ አጋርነታችሁን እንጠይቃለን፡፡
የጎህ በደምቢያ የበጎ አድራጎት ማህበር ሂሳብ ቁጥር

ኢትዮጺያ ንግድ ባንክ 1000491543136
አቢሲንያ ባንክ 61620947
ስለምታደርጉልን ቀናኢነት አብዝተን እናመሰግናለን//

አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪእናታችን ታታ መሬም ሙሃመድ ይባላሉ (የባቡ መሬም እናት ናቸው), ትውልዳቸውና እድገታቸው ደምቢያ ቆላድባ ሲሆን ትላንት፤ ያኔ፤ በዚያ በለጋ እድሜያቸው በስደት በሱዳንና...
22/02/2023

አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ

እናታችን ታታ መሬም ሙሃመድ ይባላሉ (የባቡ መሬም እናት ናቸው), ትውልዳቸውና እድገታቸው ደምቢያ ቆላድባ ሲሆን ትላንት፤ ያኔ፤ በዚያ በለጋ እድሜያቸው በስደት በሱዳንና በሳዑዲ የማይሞላውን ህይዎት ለመሙላት ታግለውታል፡፡

በኋላም "የሰው ወገን፡ ያገር ሰው ነው" ብለው ወደ ሀገራቸው በመመለስ አዲስ አበባ ኮተቤ 02 ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በጉሊት ስራ ከ3 አስርት አመታት በላይ ከበሽተኛው ልጃቸው ጋር በመሆን ከኑሮ ጋር ግብ ግብ ገጥመው ቆይተዋል፡ ኖረውማል፡፡

በዝች ከንቱ አለም "ማንም ወጣት እንደሆነ፤ የሚዘልቅ የለም"ና ይህ ጊዜያዊ የመቆያ አለም እናታችንን ላይ ታች ብለው እንዳያድሩ፡ ጤናቸውንም አጉድሎ፡ ከመስራትም አግዶ፡ ቤት እንዲውሉና የሰው እጅ እንዲጠብቁ ፈርዶባቸዋል፡፡
ወዳጆቻችን› ታዲያ እኒህን እናት በችግር ላይ መሆናቸውን በሰማን ጊዜ እኛ የጎህ በደምቢያ የበጎ አድራጎት ማህበር አባላት ያሉበት ድረስ በመሄድ ያሉበትን ሁኔታ ለመመልከት ችለናል፡፡

በመሆኑም እናታችን ታታ መሬም በፎቶ ላይ እንደምትመለከቷት የጤና መጓደል፤ አልጋ ላይ መዋል ብቻም ሳይሆን የጤና እክል ያለበት ልጃቸውን ማለትም ከአንድ ልጁና ከባለቤቱ ጋር በአሳሳቢ ሁኔታ ይገኛሉ፡፡

ምንም እንኳ "የሰው ፊት መራራ፤ ስጦታውም ላመነበት መድህን" ቢሆንም ዛሬም እንደ ትላንቱ "ለድሃ ሳንቲም ብቻ ሳይሆን፤ መልካም ቃልም መጽዋት ነው" ብለን ዛሬም ከፊታችሁ ቆመናል፡፡

እናታችንን ጠጋ ብለን በዚህ ማምሻ እድሜ ለምን ወደ ሀገር ቤት አይሄዱም? እዛ የሀገሬው ሰው ደግ ነው፣ ጥሎወት አይበላም፣ ታዲያ ለምን ወደዛ እንዲሄዱ አናመቻችም ብለናቸውም ነበር፡፡

ታዲያ እሳቸውም በአዲስ አበባ ኑሮ፣ በዚያ ርሃብ በጎዳው አንደበታቸው፣ በለሆሳስ ድምጽ፡- እኔ ዘመዶቸም አልቀዋል፤ ማረፊያም የለኝም ምናልባት ጥቂት ለምሳሌ፡- የነ አህመድ ወርቁ፣ የነ መሁባውና የነ እርዚቁ ፍትፍቴ እናቶች (የእድሜ እኩያቶቸ) ካልሆኑ በስተቀር ማን ያውቀኛል፡፡ ማንስ ይቀብረኛል፡፡ ከቻላችሁስ እርቦኛል!! ጠምቶኛል!! የቤት ኪራይ የምንከፍለው የለንም!! ክፈሉልን ብለውናል፡፡ እኛም ልጃቸው ሰርቶ መጦር የማይችል ቢሆንም ባለቤቱ ጠንካራና ጤነኛ ሴት (መስራት የምትችል መሆኗን)፣ የምትሰራው ብታገኝና የሥራ ማስጀመሪያ ቢሰጣት ሽማግሌዋንም ሆነ ባለቤቷንና ልጇን ማስተዳደር እንደምትችል ገልፃልናለች፡፡

ወንድም እህቶች የእኒህ እናት በረካና ዳዕዋ (ድኣ) ያስፈልገናል፡ ሁላችሁም እጃችሁን ዘርጉልን ስንል በፈጣሪ ስም እንጠይቃችኋለን፡፡

መርዳት ለምትፈልጉ፡
በኢትዮጺያ ንግድ ባንክ ቁጥር
1000162229994

ሽኩር ወርቁ መሸሻ (ለጊዜያዊ አገልግሎት ብቻ በሚውለው የሂሳብ ቋት መርዳት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን)

ለበለጠ መረጃ

1. የኋላሸት መንግስቴ ስ/ቁ 0911889531
2. ባንችጊዜ ማለደ ስ/ቁ 0910572645
3. ሽኩር ወርቁ ስ/ቁ 0944762078
4. ታሪኩ አያሌው ስ/ቁ 0942850460
ብላችሁ መደወል ትችላላችሁ፡፡

20/12/2022

የተከበራችሁ የደምቢያና አከባቢው ተወላጆች

አስቀድሜ በማክበር ይህን ጹሁፍ ጊዜ ሰጥተው እንዲመለከቱትና ሃሳብ እንዲሰጡበት ተጋብዘዋል፡፡

ታሪኩ አያሌው
የጎህ በደምቢያ የበጎ አድራጎት ማህበር
መስራችና አባል

* ይህ አጀንዳ የጎህ በደምቢያ የበጎ አድራጎት ማህበር መላ አባላት ጉዳይ ብቻ ስላልሆነ፣ ሃሳቡ የሌላው እህትና ወንድሞቻችን ጭምር ስለሆነ፣ ለነገው የተሻለች እንደ ስሟ ለምለም የሆነች ደምቢያን ምናልባት መፍጠር ከተቻለ እና የተሻለ አማራጭ ካለም ሃሳባችንን እንገልጽ ዘንዳ ጥሪያችን ነው፡፡

ቀን - 07/04/2015 ዓ.ም
ሰዓት ከምሽቱ - 2፡30 -4፡35
የስብሰባው ሁኔታ - ቨርችዋል
ተሰብሳቢዎች: የደምቢያ ፍሬዎች

1. ዶ/ር ነጋ ጣሴ አባተ ፡ ከባህርዳር
2. ዶ/ር መለሰ ጌጡ ፡ ከአዲስ አበባ
3. ዶ/ር አያሌው ወንዴ ፡ ከባህርዳር
4. ወ/ሮ መልሽው ደመላሽ (ኤልሳ) ፡ ከካሊፎርኒያ
5. ወንድማችን አህመድ ዋሴ ፡ ከአዲስ አበባ
6. ዶ/ር በሪሁን ፡ ከባህርዳር
7. አቶ አንሙት በለጠ ፡ ከባህርዳር
8. ወንድማችን ዲ/ን የህይስ ስብሃት (አባ ስብሃት ልጅ) ፡ ከባህርዳር
9. አቶ ቻሌ ሙላት ፡
10. አቶ በሪሁን አቡሃይ ፡ ከቆላድባ
11. ታሪኩ አያሌው ፡ ከአዲስ አበባ

አጀንዳው
እንደ ደምቢያ አንድ (1):-

* የኢኮኖሚክ ትራንስፎርሜሽን ማምጣት የሚችል፤
* ሩቅ አዳሪ፤
* ተራማጅ፤
* ችግር ፈች፤
* መንግስት የሚፈራው (ጠንካራ ለማለት የተጠቀምኩት ቃል እንደሆነ ልብ ይባል)፤
* በበርካታ ጉዳዮች ዙሪያ የሚሰራ፤
* ሁለቱን ወረዳዎች ያማከለ፤
* በሃገር ውስጥም ይሁን ከሃገር ውጭ የሚገኙ ተወላጆችን ያካተተ፤
* ጎንደር፣ ባህርዳርና አዲስ አበባ ብሎም በውጭ ሃገራት አደረጃጀት የሚኖረው ወዘተ ያማከለ በእውቀት በበለፀጉ እንቁ ልጆቿ!..

አንድ የደምቢያ ልማት ማህበር እንመስርት ብለው ተነስተዋል፡፡ ያ የልማት ማህበር ጎህ ይሁን: Social Development for Change ይሁን ወይም ሌላ ስም ይኑረው በቀጣይ ውይይት የሚደረግበት ሆኖ;

የዚህ አጀንዳ አንኳር ነጥብ እንደ ደንቢያ አንድ የልማት ማህበር ቢቋቋም ይጠቅማል ወይስ አያስፈልገንም በሚለው ላይ ያተኩራል፡- እንዴት ይደራጅ /አደረጃጀቱ ምን ይመስላል፤ ከዚህ በፊት ደምቢያ ላይ የሚሰሩ ሁለት የበጎ አድራጎት ማህበራት እንዳሉ የሚታወቅ ቢሆኑምና ውሳኔው የአባላቶቻቸው ስለሆነ በቀጣይ የማህበራቱ ውሳኔ እንደሆነ የሚታወቅ ቢሆንም፡ ለዚህ አጀንዳ ለማቋቋም /ለመመስረት ሆነ ላለመመስረት ለታሰበው ማህበር የእርስዎ ሀሳብ ገንቢ ነውና ስሜትዎትን በመግለጽ ማህበራዊ ሀላፊነትዎን ይወጡ፡፡

ጎህ በደምቢያ የበጎ አድርጎት ማህበር በቀን 25-03-2015 ዓ.ም መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል።* በውይይቱም ማህበሩ ያከናወናቸውን እና ወደፊት ሊሰሩ የታሰቡ ተግባራትን ተመልክተናል።* ሆኖም...
05/12/2022

ጎህ በደምቢያ የበጎ አድርጎት ማህበር በቀን 25-03-2015 ዓ.ም መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል።

* በውይይቱም ማህበሩ ያከናወናቸውን እና ወደፊት ሊሰሩ የታሰቡ ተግባራትን ተመልክተናል።

* ሆኖም ማህበራችን የሰራቸውና እየሰራቸው ያሉት ተግባራት እጅጉን መበረታታትና በዚሁ መቀጸል ያለበት መሆኑን።

* በቀጣይነትም ሊሰሩ ያሰብናቸው ተግባራት ከጤናና ትምህርት ሴክተር እንደተጠበቀ ሆኖ በወረዳው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ምስኪኖችን የቧንቧ ውሃ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማድረግ ስራ ከምንሰራቸው አጀንዳዎች መካከል ዋነኞቹ ሲሆን ይህንኑ እና ሌሎችም ተግባራት ለማከናወን የናንተን የተከበራችሁ የጎህ በደምቢያ የበጎ አድራጎት ማህበር ወዳጆቻችንን እገዛና እርዳታ እንሻለንና የተለመደውን ትብብራችሁን እንጠይቃለን።

ከጎናችን ስለሆናችሁም እናመሰግናለን!!

ጎህ በደንቢያ የበጎ አድራጎት ማህበር ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በተደረገለት የቁሳቁስ ድጋፍ ለምስራቅ ደምቢያ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አበረከተ!!ጎህ በደምቢያ የበጎ አድራጎት ማህ...
25/11/2022

ጎህ በደንቢያ የበጎ አድራጎት ማህበር ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በተደረገለት የቁሳቁስ ድጋፍ ለምስራቅ ደምቢያ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አበረከተ!!

ጎህ በደምቢያ የበጎ አድራጎት ማህበር ለደምቢያ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የተለያዬ የህክምና መሳሪያዎችን እና መካከለኛ ጄኔሬተር ድጋፍ አደረገ።

ማህበራችን ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሀላፊዎችን እና ባለሙያዎች ጋር በአካልና በደብዳቤ ባደረገው ግንኙነት የተለያዬ ለሆስፒታሉ የሚጠቅሙ ንብረቶችን በድጋፍ የተረከበን ሲሆን ንብረቶችም፦

1. አንድ አዲስ የፈረንሳይ ምርት መካከለኛ ጄኔሬተር
2. 4 ኮልድ ቦክስ (አዲስ)
3. 25 ዲጂታል ቴርሞ ሜትር እና 10 አክሰሰሪ
4. 9 ቴርሞ ሜትር
5. 2 አናን ኢኒስትሩመንት
6. 4 ሎግ ታግ
7. 2 ፍሪጅ ታግ ትልቁና 10 ትንሹ; ሲሆኑ ከዚህ በተጨማሪም ማህበራችን ጎህ በደምቢያ የበጎ አድራጎት ማህበር 26,700.00 በፊደል ሀያ ስድስት ሽህ ሰባት መቶ ብር ወጪ በማድረግ የገዛቸውን የተለያዬ የስኳር መለኪያ እና የደም ግፊት መለኪያዎችን ማለትም:-

1. Blood Glucose test Strip Qt 50
2. Blood Glucometer Machine Qt 1
3. Boso BS 90mm with integrated 🩺Stethoscope Qt 2
4. Boso Clinicus I blue 600mm with adult cuff Qt 3
5. Stethoscope Qt 3
6. Blood Glucometer Machine Qt 1
ለደምቢያ ሆስፒታል ድጋፍ ማድረግ ችሏል።

ንብረቶችን ከሆስፒታሉ ተወክለው ለመጡት ለአቶ መኳንንት ሽፈራው በማህበሩ አመራሮች አማካኝነት ርክክብ ተፈጽሟል።

የኢትዮጺያ ቀይ መስቀል ማህበር የሰ/ጎንደር ቅርንጫፍ የአምቡላንስ ሾፌር የነበረው መንግስት ምኒል ከአድዋ - ወልቃይት አዲረመጽ ሆስፒታል ቁስለኞችን ለማድረስ ብሎም የተለመደውን ሰብዓዊ አገል...
30/10/2022

የኢትዮጺያ ቀይ መስቀል ማህበር የሰ/ጎንደር ቅርንጫፍ የአምቡላንስ ሾፌር የነበረው መንግስት ምኒል ከአድዋ - ወልቃይት አዲረመጽ ሆስፒታል ቁስለኞችን ለማድረስ ብሎም የተለመደውን ሰብዓዊ አገልግሎት ለተጎዱ ወገኖች እገዛ በማድረግና በማሽከርከር ላይ ሳለ በታጣቂ ሀይሎች በተተኮሰ ጥይት መገደሉን የኢትዮጺያ ቀይ መስቀል ማህበር መግለጹን ተከትሎ፡

‹ ጎህ በደምቢያ የበጎ አድራጎት ማህበር› ለወንድማችን ነፍሱ በሰላም ታርፍልን ዘንዳ እንዲሁም ለቤተሰቦቹ መጽናናትን ይመኛል፡፡

መንጌ በህይዎት ሳለህ የሰራኸው ስራ ስጋዊውን ተግባር ብቻም ሳይሆን መንፈሳዊውንም ጭምር ነው!!

ይገርማል ይደንቃል፡ ሁሉም ያዝንልሃል፤
እንዴት ለበጎ ስራ፡ ሰው ወጥቶ ይቀራል፤ (ይሉሀል)
ሀገር ስላንተ ያወራል፤
በሰራኸው ስራ (እመነኝ)፡ ስምህ ገናና ነው ሲታወስ ይኖራል፡፡

23/10/2022

የለቅሶ ዜማ ግጥም
ተጻፈ ከህሩይ ወ/ስላሴ
1910 ዓ.ም
አ.አ
በኢትዮጺያ ማተሚያ ቤት ታተመ

በርሃብ ምክንያት ከጎጃም ሄደው በጎንደር አጠገብ በደምቢያ የሚኖሩ ባልና ሚስት ነበሩ፡፡ በመካከላቸው እውነተኛ ፍቅር ነበረ፡፡ እርሱ ወደ ውጭ በወጣ ጊዜ ደህና መግባቱን ትጠራጠር ነበረች፡፡ እሳቸውም እንደዚያው፡፡

ደምቢያ መልካም ሀገር ነውና እርሱ እያረሰ እርሷ እያረመች በጤና ሲኖሩ መቸም ይህ አለም የመከራ አለም ነውና ሴቲቱ ቀርታ ወንዱ ሞተ፡፡ በዚያን ጊዜ እንዲህ ብላ አለቀሰች፡-

ገብስ አርሚ ሲሉኝ ልቤ እየታከተ፤
ጤፍ አርሚ ሲሉኝ ልቤ እየታከተ፤
ነዶ አግዥ ሲሉኝ ልቤ እየታከተ፤
እንግዲህ ልረፈው መኸር ተከተተ፡፡ ብላ ሀዘኗን ገለጸች!!

›እኔም አልኩ!... ለዛሬው ግን ከለቅሶ ይሰውረን፡ ከሃዘን ይጠብቀን፡ ደግ ነገር ሰርተን ሀዘኑን በደስታ እንለውጠው፡ ከክፋት ከምቀኝነት እንራቅ፡፡ ከነዚህ ሁሉ እርቀን በደግነት ውስጥ አልፈን አይቀሬው ጥሪ ሲመጣ በደስታ ለመሄድ ያብቃን!!

ስለዚህ በደግነት ተግባር እንገኝ፡፡ ይህንንማ እናረገዋለን፡ በደግነት ተግባር ከተሰማራን ቆየን ማለታችሁን ገምቸ ደስ አለኝ፡፡ ለደስታችንም ምስጋናየን አቀረብኩ፡፡

(በታሪኩ አያሌው ተሰነናዳ)

ማህበራችን "ጎህ በደምቢያ የበጎ አድራጎት ማህበር" ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ያከናወናቸውን ተግባራት አስመልክቶ ሪፖርት ቀርቧል: የእውቅናና የምስጋና ፕሮግራምም አካሂዷል።ማህበሩ የሚያ...
10/10/2022

ማህበራችን "ጎህ በደምቢያ የበጎ አድራጎት ማህበር" ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ያከናወናቸውን ተግባራት አስመልክቶ ሪፖርት ቀርቧል: የእውቅናና የምስጋና ፕሮግራምም አካሂዷል።

ማህበሩ የሚያካሂደውን መደበኛ ስብሰባ ምክንያት በማድረግ ከዚህ በፊት ስለተከናወኑት እና እየተከናወኑ ስላሉ ስራዎች በታላላቅ ወንድሞቻችን ተጋባዥነት የእውቅናና የምስጋና ሰርትፍኬት ተበርክቶልናል።

Address

Addis Abeba
Addis Ababa
FUTUREPARK

Telephone

+251942850460

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Goh Bedembia Charitable Association posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Goh Bedembia Charitable Association:

Share