Amhara Association in QLD Australia የአማራ ማህበር በኩዊንስላንድ አውስትራሊያ

  • Home
  • Australia
  • Brisbane, QLD
  • Amhara Association in QLD Australia የአማራ ማህበር በኩዊንስላንድ አውስትራሊያ

Amhara Association in QLD Australia የአማራ ማህበር  በኩዊንስላንድ አውስትራሊያ Proud to be Amhara !

ታላቅ አለም አቀፍ የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪ ለአማራና የአማራ ደጋፊዎች በሙሉ!ጨፍጫፊው እና ፋሺስቱ የአብይ አህመድ አንባገነን አገዛዝ: በአማራ ህዝባችን ላይ ጦርነት በማወጅ፣ በአሁኑ ሰዓት በሰው...
21/10/2024

ታላቅ አለም አቀፍ የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪ ለአማራና የአማራ ደጋፊዎች በሙሉ!

ጨፍጫፊው እና ፋሺስቱ የአብይ አህመድ አንባገነን አገዛዝ: በአማራ ህዝባችን ላይ
ጦርነት በማወጅ፣ በአሁኑ ሰዓት በሰውአልባ፣ በጦር አውሮፕላን እና በከባድ መሳሪያ በመታገዝ: የሚፈፀመውን የጅምላ ዘር ጭፍጨፋ በመቃወም በመላዉ ዓለም ለወገኖቻችን ድምፅ ለመሆን!

ሰልፉ የሚደረግባቸው የዓለም ከተሞች ፣

1. Berlin, Germany: October 18, 2024
2. Indianapolis, USA: October 25, 2024
3. Frankfurt, Germany: November 9, 2024
4. Paris, France: November 9, 2024
5. Stockholm, Sweden: November 9, 2024
6. Queensland, Australia: November 9, 2024
7. London, UK: November 10, 2024
8. Washington, D.C., USA: November 10, 2024
9. Pretoria, South Africa: November 10, 2024
10. Minnesota, USA: November 10, 2024
11. Brussels, Belgium: November 10, 2024
12. Geneva, Switzerland: November 12, 2024
13. Oslo, Norway: November 23, 2024

አዘጋጅ: ዓለም አቀፉ የአማራ ግብረሃይል

12/01/2024

የኢትዮጵያ ገጽታ እንደዚህ ዘመን አስቀያሚና ደካማ ሆኖ አያውቅም። በሁሉ ነገር ዘቅጠናል። የሀገራት ጭራ ሆነናል። ተደማጭነታችን ከዜሮ በታች ወርዷል። እንደዚህ አገዛዝ የኢትዮጵያን ዲፕሎማሲ አረንቋ ውስጥ የከተተ የኢትዮጵያ መንግስት አልነበረም። አብይ የሚሉት ደመነፍሳዊ ገዢ ሀገሪቱን የእንፉቅቅ እያስኬዳት ለመሆኑ አንዱ ማሳያ በውጭ ጉዳይ ገጽታችን ላይ የደረሰብን ስብራት ነው።

መደመር በሚሉት ቅጣንባሩ በጠፋና በቅዠት ላይ በተቸነከረ አስተሳሰብ የተለወጠው የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ከሀገራት ጋር አናጭቶን፥ ከሁሉም አጋጭቶን፡ በአፍሪካው ቀንድ ከአንድም ሀገር ጋር መልካም ወዳጅነት እንዳይኖረን አድርጎ ያስቀረን እንደሆነ በግልጽ የምናየው ጉዳይ ነው።

ታላቅ ህዝብ ታላቅ ሀገር ይዘን የአንዲት አረብ ሀገር አሽከርና ቅጥረኛ እንድትሆን ቀን ከሌሊት የሚሰራ ደካማ ሰው እጅ ላይ ወድቀናል። በድግስና ግርግር የሚመጣ ለውጥ የለም። በየዕለቱ ፌሽታና ቸበርቻቻ የትም አያደርስም። ይህ አገዛዝ ስለውጭ ጉዳይ አፉን ሞልቶ ለመናገር የሚያስችል ሞራል የለውም። አሳማን ከንፈሯን ሊፒስቲክ ቢቀቧት መቼም ቆንጆ አትሆንምና።

01/01/2024

አዲስ ዓመት አምሽቼ ስለነበር እንቅልፍ ጥሎኝ አረፋፍጄ ነበር የተነሳሁት። ከአልጋዬ ሳልወርድ የእጅ ስልኬን አነሳሁና ዓለም እንዴት እንዳደረች ለማየት የማህበራዊ መድረክ ገጾቼን ገልመጥ ገልመጥ አደረኩ። ወረራ የተፈጸመባቸው ይመስል በብልጽግና ሰዎች የእንኳን ደስ ያለን መልዕክት ተጥለቅልቋል። ምን ተገኘ? ከደስታው ተካፋይ ለመሆን🤣🤣ጥረት አደረኩ። በጽሁፍ የተቀመጠ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አንዲት ንግግር ላይ ዓይኔ አረፈ። ''ፈጣሪ ይመስገን እንጂ ሌላ ምን ሊባል ይችላል?'' ይላል። ጉጉቴ ጨመረ። የብልጽግና መንደር በከበሮ ደምቋል። ግሪሳው ጮቤ እየረገጠ ነው። በውስጥ መስመር ሳይቀር ''አንጀታችሁ ቅጥል ይበል፥ ብልጽግናችንን ልናረጋግጥ ከጫፍ ደርሰናል'' የሚል ይዘት ያላቸው መልዕክቶች ከዚሁ መንደር ሰዎች ተልኮልኛል። አረ! ግድየለም። ይሄ ነገር ፔትሮ ነዳጅ የእውነት ተገኝቶ ይሆን? ከመልዕክት ሳጥን ውስጥ ወጣሁና ወደ ገጾቹ ተመለስኩ።

''በኢትዮጵያና በሶማሌላንድ መሀል የባህር በር ተጠቃሚኒት ላይ የመግባቢያ ሰነድ ፊርማ ተከናወነ''

ዜናው ይሄ ነው። ሌላ ነገር ብፈልግ ባስስ ምንም አልታይህ አለኝ። ወዳጆች ጋር ጻፍኩኝ። ደወልኩኝ። ከዚህ ውጪ ምንም ነገር እንዳልሰሙ ነገሩኝ። እንዴ ጎበዝ?! ምንድን ነው ነገሩ? ይሄ ሁሉ ከበሮ ድለቃ ለዚሁ ነው? ጮቤ መርገጡ ለመግባቢያ ሰነድ ፊርማው ነው? የጠቅላይ ሚኒስትሩ ''ፈጣሪ ይመስገን....'' መልዕክት፥ የሬድዋን ሁሴን ''ወታደራዊ ቤዝ.....'' የካድሬው ቡረቃ፥ የቴሌቪዥኑ ጩኸት፥ ይህ ሁሉ ግርግር የመግባቢያ ሰነድ መፈራረሙ ነው?

አንድ ነገር በአእምሮዬ ተከሰተልኝ። የባህር በር ባለቤት የሚለው የአብይ አህመድ አጀንዳ ብዙም ርቀት ሊወስድ ባለመቻሉ በዚህች ግርግር ያሰብነውን አሳክተናል የሚል መግለጫ በቅርቡ ልንሰማ እንችላለን። በዚህ ቢሉ በዚያ ቢያማትሩ የትኛውም የቀጠናው ሀገራት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ''የባህር በር ባለቤትነት'' ፉከራ እጅ ሊሰጡ፡ ሊስማሙም የሚችሉ አልሆኑም። የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት አብይ አህመድን እክ እንትፍ ብለው ተፉት። አገለሉት። ብቻውን ቀርቷል። በጉልበትም አስቦ ነበር። ፌንጣ ብትቆጣ አንድ እግሯን ታጣ ሆነበትና ፎክሮ፡ አቅራርቶ ትቶታል። አጀንዳውን መዝጋት ስለሚያስፈልግ በዓለም ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ህጋዊ ቁመና የሌላትን ሀገር ደጅ ጠንቶ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ። ይሄም ቢሆን ገና ነው። ብዙ ብዙ ነገሮች መደረግ አለባቸው። ከመሆን ይልቅ ያለመሆን እድሉ የሰፋ ነው። ተስፋ ማድረጉ አንድ ነገር ነው። የሆነ ያለቀ ያበቃ፡ ኢትዮጵያ የባህር በር ያገኘች አስመስሎ ''ፈጣሪ ይመስገን'' ምናምን የሚያስብል አይደለም። ህዝብ ማደናገርና ማጭበርበር የብልጽግና አገዛዝ ዋና መገለጪያው ስለሆነ እንጂ የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ከአንዲት ብጣሽ ዜና የምታልፍ አይደለችም።

የመግባቢያ ሰነድ ከሌሎች ሀገራት ጋርም መፈራረም ይቻላል። ተፈራርመዋልም ይመስለኛል። አዲስ ነገር አይደለም። እንዲህ ሀገር ምድሩን በጩኸትና በግርግር የሚያምስ አይሆንም። ብልጽግናዎች የተቀባይነት ቀውስ ገጥሟቸዋል። ህዝብ አንቅሮ ተፍቷቸዋል። ከዚህ በኋላ የኢትዮጵያን ምድር በዕንቁ አልማዝ ቢሞሉ፡ በየቤቱ ወተት በቧንቧ ቢያቀርቡ እንኳን የሚቀበላቸው የለም። አራት ክልሎች ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ያልቻለውና ምስጥ እንደበላው ኩይሳ ተቦርቡሮ ያለቀው የአብይ አህመድ አገዛዝ ''ቲማቲም ተመረተ፥ የአገዳ እህል ተሰበሰበ'' ዓይነት ጨው ጥቅሙና ጉዳቱ ይዘት ያላቸውን ዜናዎች በሰበር ቢነግረን፥ ከበሮ እየደለቀ ያዙኝ ልቀቁኝ ቢል አልፈርድበትም። የወደቁ ግፈኛ አገዛዞች በመጨረሻው ሰዓት እንዲህ አድርጓቸዋልና።

Mesay Mekonen

ሠበር የጀብድ ዜናበ50 አለቃ ወንድሙ ማሩ  የሚመራው💪 የላስታ አውራጃ ብ/ጄኔራል አሳምነው ፅጌ  #ክፍለጦር በታህሳስ 14/2016ዓም ከጧቱ 3:00 በአንድ ሲኖ ትራክ፣ በሁለት ኦራል እና በ...
29/12/2023

ሠበር የጀብድ ዜና

በ50 አለቃ ወንድሙ ማሩ የሚመራው💪

የላስታ አውራጃ ብ/ጄኔራል አሳምነው ፅጌ #ክፍለጦር በታህሳስ 14/2016ዓም ከጧቱ 3:00 በአንድ ሲኖ ትራክ፣ በሁለት ኦራል እና በአንድ Iveco ትራክ ሙሉ ተጭኖ ከላሊበላ ወደ ቡግና ሲጓዝ የነበረ የጠላት አብይ ጦር ልዩ ቦታው ገንጅ የተባለውን ቦታ አለፍ ብሎ "መስኮይ" ከምትባል ቦታ በነበልባሎቹ የጀግናው የአሳምነው ፅጌ ልጆች በተፈፀመ መብረቃዊ የደፈጣ ጥቃት በአራቱም ከባድ መኪኖች ላይ ተጭኖ የነበረው ግዑዛን የጠላት አብይ ጦር ሙሉ ለሙሉ መደምሰስ ሲቻል መኪኖቹ ሲቃጠሉ የተወሰኑ ዘመናዊ የነፍስ ወከፍ እና የቡድን መሳሪያዎችን ማግኘት ተችሏል። አሁን በዚህ ስዓት ተጨማሪ እሬሳ አንሽ ኃይል በማምጣት እሬሳውን ሲለቅም ገዥ ቦታዎቻችንን ይዘን እያየነው ነው ብለዋል።

መንገሻ ፈንታው የክልሉ ኮሙኒኬሽን "ፋኖን ከገባበት ገብቶ መከላከያችን ይበቀለዋል" ብሎ በዛተው ዛቻ መሰረት ህዳር 19/2016ዓም በድሮን ጥቃት ወገኖቻችንን መጨፍጨፉ ይታወቃል ይህ የዛሬው በጠላት ላይ የተፈፀመው የደፈጣ ጥቃት ከ120 በላይ ቲማትምን ስናፈርጠው ለድሮን ጥቃቱ የተሰጠ መልስ መሆኑን ደም መላሾቹ የጀግናው የአሳምነው ፅጌ ልጆች ገልፀዋል።

አሳምነውዊዝም ብቸኛ የመዳኛ
መንገዳችን ነው!!!!

28/12/2023

በወልዲያ በነበልባሉ ፋኖ የተገደለው ጀነራል ..‼️‼️

የአብይ ወታደራዊ ጄኔራል ወልዲያ ላይ በፋኖ ሃይል ተገደለ ! .......... በኦሮሚያ ክልል በተካሄደ የአመራሮች ስብሰባ አማራው የድሮውን ስርዕት ሊጭንብን ስለመጣ የኦሮሞ ሕዝብን ተነስ ብላችሁ ቀስቅሱት የሚል መመሪያ ተሰቷል። .......... በአንድ ከፍተኛ የአብይ አሕመድ ዲፕሎማት ከዳ። ....... ሰሜን ሸዋ የፋኖ ሃይል በደራ በኩል በተካሄደ ውጊያ ትልቅ ድል ተገኝቷል። ........

በሁለት ወቅታዊ ጉዳዮች ከአማራ ፋኖ የደህንነት ክንፍ የተሰጠ መግለጫ ..‼️‼️የአማራ ሕዝብ በተለይ ባለፉት 6 ዓመታት መንግሥት መር ጭፍጨፋ እየተፈፀመበት ይገኛል። ይህ ጭፍጨፋ ጅማሮውን ከ...
27/12/2023

በሁለት ወቅታዊ ጉዳዮች ከአማራ ፋኖ የደህንነት ክንፍ የተሰጠ መግለጫ ..‼️‼️

የአማራ ሕዝብ በተለይ ባለፉት 6 ዓመታት መንግሥት መር ጭፍጨፋ እየተፈፀመበት ይገኛል። ይህ ጭፍጨፋ ጅማሮውን ከኦሮሚያ ክልል በማድረግ በርካታ ሺዎችን አማራዎችን ጨፍጭፎና ሚሊዮኖችን አፈናቅሎ በመጨረሻም ወደ አማራ ክልል በመግባት ይህንኑ ህልሙን ለመፈፀም አቅዶ እየሰራ ይገኛል።

የአማራ ፋኖም መላው ህዝባችን በማስተባበር ይህን ፋሽስታዊ ስርዓት ከእነ እቅዱና አስተሳሰቡ ለመቅበር ትግል ከጀመረ በርካታ ወራቶች ተቆጥረዋል። በዚህ ያለፉት ወራቶች የትግል ሂደትም የክልሉን መንግሥት ምላሱ ብቻ የቀረ አየር ላይ የሚንሳፈፍ ፍጥረት ማድረግ ከመቻሉም በላይ የአገዛዙ የጭቆና አስፈፃሚና የጭፍጨፋ ተዋናይ የሆነውን ሰራዊት በተገቢው መልኩ ማመናመን ተችሏል።

ይህ በእንዲህ እያለ በአሁኑ ወቅት ቅርቃር ውስጥ ያለው ፋሽስታዊው አገዛዝ በሕዝባችን ላይ በእጅ አዙር እየፈፀማቸው ያሉ ሴራዎች በመኖራቸው ምክንያት በሚከተሉት ሁለት ጉዳዮች ዙሪያ አስቸኳይ መግለጫ መስጠት አስፈላጊ ሆኗል።

1ኛ) ፋሽስታዊው አገዛዝ በአማራ ክልል በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ (ሃሰተኛ የብር ኖቶችን ጨምሮ) በመመደብ ጤፍና ሌሎች እህሎችን በመሰብሰብና በተለያዩ ማዕከላት በማሰባሰብ ሰውሰራሽ እጥረት ለመፍጠርና የአማራ ገበሬዎችንና ነጋዴዎችንም ለኪሳራ፣ አጠቃላይ ሕዝቡን ደግሞ ለርሃብ ለመዳረግ እየተሰራ እንዳለ ተረድተናል።

በመሆኑም ይህ የሴራው ትብታብ እስኪበጣጠስና ወደ ክልሉ የገባው ሃሰተኛ ኖቶች መዳረሻ እስኪታወቅና እስኪሰበስብ ድረስ ከክልሉ የሚወጣ ምንም አይነት እህል እንደማይኖር እናሳውቃለን። በዚህ ተግባር ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎችና የአሽከርካሪ ባለቤቶችም ንብረታቸው እንደሚወረስ እንደሚወርስ እናስታውቃለን፤ በዚህ ተግባር ተሳትፎ ባላቸው ማንኛውም አካላት ላይም ጥብቅ እርምጃዎችንም የምንወስድ ይሆናል።

2ኛ) በክልሉ በተለያዩ ከተሞች የመሬት ሊዝ ጨረታዎች በማውጣት አገዛዙ ሕዝብን መጨፍጨፊያ ከፍተኛ ለመሰብሰብ አቅዶ እየሰራ እንደሆነ አውቀናል። እስከአሁንም በባሕር ዳርን፣ በደሴ፣ በደብረ ማርቆስና በሌሎች ትላልቅ ከተሞች የሊዝ ጨረታዎች መውጣታቸው ታውቋል። ይህ የአገዛዙ አካሄድ እራሱን በገንዘብ በማደርጀት በሕዝባችን ላይ የሚፈፅመውን ጭፍጨፋ ለማጠናከር ያለመ ነው። በመሆኑም በሊዝ ጨረታው ባለመሳተፍ እራስን ከኪሳ ከማዳን ባለፈ ለአገዛዙ ጉልበት እንዳትሆኑ ስንል ለመላው ለሕዝባችን መልዕክት እናስተላልፋለን። ይህን ጥሪ ሳይቀበል ገፍቶ የሚሄድ ግለሰብ በቀጣይ ለሚያጋጥመው ኪሳራ ኃላፊነቱን እራሱ የሚወስድ ይሆናል።

እነዚህን ሁለት የመግለጫው አካል የሆኑ ሁለት መመሪያዎች ሕዝባችንና መላው የፋኖ መዋቅር በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲፈፅምና እንዲያስፈፅም እናሳስባለን።

ታህሳስ 17/2016 ዓ.ም

29/11/2023
  ! ከልጅ እያሱ ክፍለ ጦር የተሰጠ መግለጫ ..‼️‼️የገጠመንን የህልውና ትግል ቀልብሰን ህዝባችን ለመታደግ ነፃነታችንን በክንዳችን ለማረጋገጥ ታሪካችን በእጆቻችን ለመፃፍ አንድ ሆነን ከመ...
28/11/2023

! ከልጅ እያሱ ክፍለ ጦር የተሰጠ መግለጫ ..‼️‼️

የገጠመንን የህልውና ትግል ቀልብሰን ህዝባችን ለመታደግ ነፃነታችንን በክንዳችን ለማረጋገጥ ታሪካችን በእጆቻችን ለመፃፍ አንድ ሆነን ከመታገል ውጭ ሌላ አማራጭ አለመኖሩን አውቀን አንድነታችን አጠንክረን ጠላቶቻችን እንዳሰቡት ሳይሆን በተቃራኒው ድልን እየተቀናጀን እንገኛለን።ስለሆነም አጠቃላይ በደቡብ ወሎ ዞን ወረዳ ውስጥ የሚገኙ የፋኖ አደረጃጀቶች በብርጌድ ተደራጅተው ወደ አንድ ክፍለ ጦር በመምጣት የልጅ እያሱ ክፍለ ጦር በሚል ተቋቁሟል።

በዚህ መሰረት የልጅ እያሱ ክፍለ ጦር የጋራ ስራ አስፈፃሚ በማዋቀር ሰባት ብርጌዶችን በመያዝ መመስርት ችሏል።
የብርጌዶቹ ስምና የሚቀሳቀሱበት ቦታ እንድሁም አዛዥና ምክትል አዛዥ እንደሚከተለው ተቀምጠዋል።

1.ንጉስ ሚካኤል ብርጌድ
ዋና አዛዥ ፋኖ ሰለሞን አሊ
ምክትል አዛዥ ፋኖ አብይ ከበደ
የሚንቀሳቀስበት ቀጠናና
1.ደሴ ከተማ
2.ደሴ ዙሪያ ወረዳ
3 አልብኮ ወረዳ
4 ኩታበር ወረዳ
5.ኮምቦልቻ

2.አሳምነው ብረጌድ
መሪ ፋኖ ዶክተር ሙሉጌታ ድጋፌ
ምአዛዥ ሙሉጌታ የሺጥላ

የሚቀሳቀስበት ቀጠባ
1.አማራ ሳይንት ወረዳ
2.ሌጋምቦ ወረዳ
3.ቦረና ሳይንት ብሄራዊ ፓርክ

3.መቅደላ ብረጌድ
ዋና አዛዥ 50 አለቃ ሰይድ ሙሀመድ
ም/አዛዥ 10 አለቃ ጌትነት ታደሰ
የሚሽፍኑት ቀጠና
1. ማሻ ወረዳ
2. ተንታ ወረዳ
3.ቱላአውሊያ /ጊምባ

4.ሚንሊክ ብርጌድ
ዋና አዝዥ ፋኖ አብነው ታደሰ
ምክትል አዛዥ መቶ አለቃ በላይ መከተ
የሚንቀሳቀስበት ቀጠና
1.መካነሰላም (ቦረና) ወረዳ
2.ወግድ ወረዳ
3.ከለላ ወረዳ

5.ታዘበው ብረጌድ
ዋና አዛዥ ኑረድን
ምክትል አዛዥ ወልደ ታደሰ
የሚቀሳቀስበት ቀጠና
1,ጃማ ወረዳ
2,ወረኢሉ ወረዳ
3.ደገር
4.ለገሂዳ ወረዳ

6.ቴዎድሮስ ብርጌድ
ዋና አዛዥ ፋኖ አባተ ካሳነህ
ም/አዛዥ 100 አለቃ ተገኔ አለባቸው
የሚቀሳቀስበት ቀጠና
1.ኮምቦልቻ ከተማ
2.ተሁለደሬ ወረዳ (ሀይቅ)
3.ቃሉ ወረዳ
4 አምባሰል ወረዳ
5.ደላንታ ወረዳ

7.አትሮንስ ብርጌድ
ዋና አዛዥ ይታገስ አራጋው
ምክትል አዛዥ ሻምበል ጀምበሩ
የሚቀሳቀሳበት ቀጠና
1.መሀል ሳይንት ወረዳ
2.ቦረና ሳይንት ብሄራዊ ፓርክ
3.ሌጋምቦ ወረዳ

በዚህ አደረጃጀት ውስጥ የአማራን ህዝብ ህልውና ለማስከበር እና የመጣብንን ፈተና ለመቀልበስ እንድሁም አብሮን ለመታገል የሚፈልግ አካል በብርጌድ፣ በሻለቃና በሻምበል እየተዋቀረ ለሚመጡ እና አብሮን ለስራት ፋላጎት ያለው ሁሉ አብረን ለመስራት በራችን ክፍት መሆኑንና በክፍለ ጦሩ ስር ለመካተት ፍቃደኝነታችን ከወደሁ ለማሳወቅ እንወዳለን።

ድል ለአማራ ህዝብ
ዘላለማዊ ክብር ለትግሉ ሰማእታት‼️

20/11/2023

እየመጡ ነው እየመጡ ነው .....!

ድል ለፋኖ !!

የዐማራ ማኅበር በኩዊንስላንድ አባላት እና ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ከዘመን ዘመን አሸጋገራችሁ መልካም አዲስ ዓመት ይሁንላችሁ! 2016 ዓ/ም የሕዝባችን የድል ዓመት ይሁንልን!
11/09/2023

የዐማራ ማኅበር በኩዊንስላንድ አባላት እና ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ከዘመን ዘመን አሸጋገራችሁ መልካም አዲስ ዓመት ይሁንላችሁ! 2016 ዓ/ም የሕዝባችን የድል ዓመት ይሁንልን!

Address

Brisbane, QLD
4169

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Association in QLD Australia የአማራ ማህበር በኩዊንስላንድ አውስትራሊያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Featured

Share